የልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ ቤተሰቦች ጥያቄ እና የንጉሣውያኑ ቤተ መንግሥት ምላሽ

በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከአባቱ ሞት በኋላ ወደ እንግሊዝ የተወሰደው ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ፣ ቤተሰቡን እና አገሩን ድጋሚ የማየት ዕድል ሳይገጥመው ነበር ሕይወቱ እዚያው በለጋነት ዕድሜው ያለፈው። ሥርዓተ ቀብሩም የብሪታኒያ ነገሥታት ከሚያርፉበት ለንደን ከሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ተፈጽሟል። የልዑሉ ህልፈት በርካታ ትውልዶችን ያሳለፈ ቢሆንም ቤተሰቦቹ እና ኢትዮጵያው…