የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አቋቁመናል ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት በቅርቡ 10 ኤጲስ ቆጶሳት እንደሚሾሙ እየገለጹ ነው !

ሌላኛው የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ችግር የሆነው እና በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የራሳችንን ቤተ ክህነት አቋቁመናል የሚሉት እነ ብፁዕ አባ መርሐክርስቶስ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በቅርቡ 10 ኤጲስ ቆጶሳትን እንሾማለን በማለት መግለጻቸውን ድምጺ ወያነ የተባለ እና በትግራይ ክልል መቀመጫውን ያደረገ የሚዲያ ተቋም ዘግቧል።

በቅርቡም 10 ኤጲስ ቆጶሳትን በአገር ውስጥና በውጭ እንደሚሾም የተናገሩት ሊቃነ ጳጳሳቱ አዲሶቹ ተሿሚዎች በቅርብ ጊዜ ውስጥም ወደ ሥራ ይገባሉ ሲሉ ገልጸዋል።

ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጭ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት በትግራይ የሚገኙት ሊቃነ ጳጳሳት መሥርተነዋል ያሉትን ቤተ ክህነት ካቋቋሙበት ጊዜ ጀምሮ ስለ ኤጲስ ቆጶሳት ሢመት ጉዳይ ያሉት ነገር ባይኖርም በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያን ያለችበትን አሁናዊ ችግር ከግምት ባላስገባ መልኩ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ ኤጲስ ቆጶሳትን ለመሾም እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ መግለጻቸው በርካታ ኦርቶዶክሳውያንን እያስቆጣ ይገኛል።

በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ጠቅላይ ጽ/ቤትም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤትን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ምንጭ:- ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

Image

Image

 

Image