የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ ወሰነ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከሳምንት በላይ በተራዘመው ስብሰባው ብዙ ባነጋገረው የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ላይ ውሳኔ ማሳለፉን ሰኞ አመሻሽ ላይ አሳወቀ። ባለፉት ወራት በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ከተከሰተው ችግር ውስጥ ዋነኛ ጉዳይ የነበረው ሹመት ጉዳይ የሲኖዶሱ ጉባኤ የመጨረሻ አጀንዳ ሆኖ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ዘጠኝ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ መወሰኑ ተገልጿል።…