
አቶ ግርማ የሺጥላ በጥይት ተደበደበ። የአቶ ግርማን ግድያ ጠ/ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
የብአዴኑ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ሃላፊ ግርማ የሺጥላ በጥይት ተደብድቦ መሃል ሜዳ ሆስፒታል መግባቱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።
ጉዳቱ የደረሰው በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ መሃል ሜዳ ከተማ ስብሰባ አድርገው በመመለስ ላይ ባሉበት ወቅት መሆንም ታውቋል።
ግርማ የሺጥላ በህይወት ስለመትረፉ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም የሚሉት ምንጮቹ የዞኑ አስተዳዳሪን ጨምሮ አብረውት የነበሩት በሙሉ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ይናገራሉ።
የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ ” ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል። ” ብለዋል።

” ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር፣ ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው። ” ሲሉ አክለዋል።
ጉሳ በምትባለው አካባቢ ከደቂቃዎች በፊት በተፈጸመው በዚህ ጥቃት በህይወት ላይተርፍ ይችላል የተባለውን ግርማ የሺጥላን ወደ ሌላ ሆስፒታል ለማዛወር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ምንጮቹ ተናግረዋል።
ምንጭ Ethio 360