ትግራይ ዉስጥ በኤርትራ ወታደሮች ስለተፈፀመ ግድያ የዓይን እማኝ መረጃ

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)የሰላም ስምምነት ከመፈራረማቸው ከሳምንት በፊት የኤርትራ ወታደሮች አድዋ አካባቢ በምትገኘው በማርያም ሸዊቶ መንደር በትንሹ 300 ሰዎች መገደላቸዉን አንዲት የመንደርዋ ነዋሪ ተናገሩ። ወይዘሮዋ የ 70 ዓመቱ ባለቤታቸዉና የ28 ዓመቱ ልጃቸዉ በኤርትራ ወታደሮች ተገድለዉባቸዋል።…