ከትግራይ ብቻ ሳይሆን ከወልቃይት ጠገዴ አካባቢ መከላከያ ሰራዊት እንዲወጣ እየተደረገ ነው

ከመከላከያ ሰራዊቱ አመራር ፍላጎት ውጭ ሰራዊቱ እንዲወጣ እየተደረገ ነው።

በሰላም ስምምነቱ መሰረት የመከላከያ ሰራዊቱ የትግራይ አካባቢዎችንም መቆጣጠር ነበረበት። ይሁንና ከትግራይ ብቻ ሳይሆን ከወልቃይት ጠገዴ አካባቢም ሰራዊቱ እንዲወጣ እየተደረገ ነው።

ህዝብ የጠላትን ከፍተኛ የወረራ ዝግጅት በየቀኑ ስለሚታዘብ፤ “ከአካባቢው ሠራዊት ሊጨመር እንጂ ሊቀነስ አይገባም” በማለት ለፌደራል መንግሥትና ለመከላከያ ሠራዊት አባላት ተደጋግሚ አቤቱታ አቅርቧል፡፡ የመከለካያ መኮንነኖች ሳይቀሩ የህህነግን የወረራ እንቅስቃሴ ስለሚያውቁት ሠራዊቱ መቀነስ እንደሌለበት ለፌደራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች አመልክተዋል፡፡ የአማራ ክልል መንግሥትም እንዲሁ በተደጋጋሚ አሳስቧል፡፡ ሆኖም በጠ/ሚው ውሳኔ ሠራዊቱ ከወልቃይት ጠገዴና ከሰሜን ጎንደር እንዲወጣ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ይህ እጅግ አደገኛ ነገር ነው፡፡ ትህነግ እድል ተሰጥቶት ሌላ ወረራ እንዲፈፅም እየተደረገ ነው። ቀጣዩ ግጭት አገርም እንዲያፈርስ የሚያደርግ ዕብደት ተብሎ ሊገለጽ የሚችል ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡

ይህ ነገር አሁንም መቆም ይኖርበታል፡፡ ሕዝቡ ሰራዊቱ እንዳይወጣ እየጠየቀ ነው፡፡ መታወቅ ያለበት ሰራዊቱ ከትግራይም ሆነ ከአማራ ክልል መውጣትን ተቃውሞ ነበር። ይህ ውሳኔ የውጮቹን ለማስደሰት ሲባል በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተደረገ ነው። የአማራ ህዝብና ፀጥታ ኃይል ራሱን ቀርቶ አገር የጠበቀ ነው። ይጠብቃልም። የመከላከያ ሰራዊቱንም ከጥቃት ያዳነ ነው። ለትህነግ የሚያንስ አይደለም። እሳቤው ግን አደገኛ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ህዝብን ከጥቃት የመከላከል ግዴታ አለበት። በስምምነቱ መሰረት ከወልቃይት ቀርቶ ከትግራይ መውጣት የለበትም። ህዝብ ሰራዊቱ እንዳይወጣ በሚያደርግበት ወቅትም ችግሮች ቢፈጠሩ ተጠያቂው መንግስት መሆኑ መታወቅ አለበት።

እንዲፈጠር የተፈለገው ሌላ ጦርነት አገር ያፈርሳል እንጅ የአማራ ህዝብ የራሱን ወገን አሳልፎ የሚረጥበት ሁኔታ አይኖርም።