ሸገር ከተማ የተቋቋመው በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉትን ኦሮሞ ያልሆኑትን ነዋሪዎች ለማፈናቀል ነው፤ ተፈናቃይ ሕጻናት በጅብ እየተበሉ ነው ።

[addtoany]

ሰሞኑን ሸገር ከተማ መቋቋም ጋር በተያያዘ በርካታ ነዋሪዎች ቤታቸው በህገወጥነት ስም ለብዙ አመታት ከኖሩበት ሰብዓዊነት በጎደለው መልኩ እየተፈናቀሉ ነው። ለአብነት ለመጥቀስ ቤታቸው የፈረሰባቸው ህፃናቶች በጅብ እየተበሉ ይገኛሉ።

በጅብ የተበላው የ4 አመቱ ልጅ

“እናቱ እስካሁን እራሷን አታውቅም!”

በታክሲ ወደ ጣፎ እየተጓዝኩ አንድ ተሳፋሪ እያለቀሰች እንባዋን በለበሰችው ልብስ ስትጠርግ የተመለከታት አጠገቧ የተቀመጣ ጎልማሳ ሰውዬ ምን እንደሆነች ይጠይቃታል። ገዋሳ የጓደኛዋን ልጅ ጅብ በልቶባት ለቅሶ እየሄደች ስለመሆኑ ትነግረዋለች። ሰውዬው እያለቀሰ ጮክ ብሎ መራገም ሲጀምር እኔን ጨምሮ ሁሉም ሰው ሰማ! ግማሹ ያመነ አይመስልም ውሸቷን ነው ይላል። ገሚሱ ያለቅሳል።
ለሳምንታት በኖረችበት ሸራ ጎጆ ውስጥ ሌሊት እንደወሰደባት ጨምራ ስትነግረን የተጠራጠሩትም ማልቀስ ጀመሩ። አሁን ሁሉም እኩል ሲያለቅስ ግማሹ በየፌርማታው ወረደ።

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ዙሪያ በጅምላ ከፈረሱ ቤቶች ጀርባ ገና ብዙ ያልተሰሙ በደሎች ይነገራሉ።

https://youtu.be/YBdfO-lolgQ