የኦሮሞ ብሄረተኝነትና ተስፋፊነት ለሚሊዮኖች መፈናቀል ምክንያት ነው #ግርማ ካሳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በለማ ቲም የሚመራው የለውጥ እንቅሳሴ ከመጣ በኋላ በአገራችን ያለው ትልቁና ዋናው ችግር የኦሮሞ ተስፋፊ ብሄረተኝነት እንደሆነ ደጋግሜ ጽፊያለሁ። ይሄን ብሄረተኝነት ከማንም በላይ የጎዳውም የኦሮሞ ማህበረሰብን ነው።

የኦሮሞ ብሄረተኞች ፣ የኦሮሞ ነው የሚሏቸው ቦታዎች ትንሽ አይደሉም። ኦሮሞዎቹ የኦሮሞ ነው እንደሚሉትም ሌሎችም አሁን ኦሮሞ ክልልው ውስጥ ያሉ አንዳንድ ቦታዎችን የኦሮሞ አይደለም የኛ ነው የሚሉም አሉ።በምሳሌ ለማስረዳት እሞክራለሁ።

የኦሮሞዎ ብሄረተኞች፡

፩. አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት፣ በኦሮሞ ክልል ስር ሙሉ ለሙሉ መሆን አለባት” ይላሉ።
፪. ሙሉ ለሙሉ የሃረርና የድሬዳዋ ከተሞች ፣ ከሶማሌ ክልል በርካታ መሬቶች ከደቡብ ሽንሌ/ሲቲ ዞን፣ ከምእራብ ፋፋንና ኖጎግ ዞኖች ወደ ኦሮሞ ክልል ምስራቅ ሃረርጌ ዞን እንዲጠቃለል ይፈልጋሉ።
፫. የተወሰኑ መሬቶች ከሶማሌ ክልል ምእራብ አፍዴር ዞን፣ የሊበንና የዳዋ ዞን ሙሉ ለሙሉ (የሞያሌን ከተማ ጨምሮ) ወደ ኦሮሞ ክልል እንዲዞር ይፈልጋሉ።
፬. በምስራቅ ወለጋና በምእራብ ወለጋ መካከል ያለው አብዛኛው ጉሞዞች በብዛት የሚኖሩበት የቤነሻንጉል ክልል ከማሽ ዞን ወደ ኦሮሞ ክልል እንዲጠቃለል ይፈልጋሉ።

አዲስ አበባ የኛ ነው የሚለው ድፍረታቸው በአዲስ አበባ ህዝብ ከፍተኛ ወገዛ ያስከተለባቸው ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ራሷን በራሷ ከማስተዳደር አልፋ የራሷን እድል በራሷ እንድትወሰን ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። አዲስ አበባን የኦሮሞ ለማድረግ የአዲስ አበባን ዲሞግራፊን ለመቀየር፣ የኦሮሞ ብሄረተኞች እነ ዶ/ር አብይን ውስጥ ውስጡን አስገድደው ያስቀመጡት ታከለ ኡማ፣ ከፍተኛ ተቃዉሞ እየደረሰበት በመሆኑ እንዲያፈገፍግ የተደረገበት ሁኔታ ነው ያለው። በሸገር ረገድ የኦሮሞ ብሄረተኞች መቶ በመቶ የፖለቲክ ሽንፈት ተከናንበዋል ማለት ይችላል።

በሌሎች ቦታዎች ግን ከፍተኛ ቀውስ የተፈጠረበት ሁኔታ ነው ያለው። በሃረርጌ፣ በቦረና ጉጂና ባሌ በኦሮሞ ብሄረተኞች፣ “መሬቱ የኦሮሞ ነው” በሚል እንቅስቃሴ ምክንያት መጠነ ሰፊና በጣም አስከፊ የጎሳ ግጭት ተቀስቅሰዋል። በኔኒሻንጉል ኦነጎች በከፈቱት ጥቃት ምክንያት ከጉሞዞች ጋር በተፈጠረው ግጭት ብዙ እልቂትና የሰው ህይወህት መጥፋትና መፈናቀል ተከስቷል።

በነዚህ ሶስቱ አካባቢዎች ብቻ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ኦሮሞዎች ወደ አራት መቶ ሺህ የሚጠጉ ሶማሌዎች ከቅያቸው ተፈናቅለዋል።

አሁን ያለው የጎሳ አወቃቀር ካልተቀየረና ሁሉም እኩል የሆኑበት አስተዳደር ካልተመሰረተ፣ አሁን ባለው እንቀጥል ከተባለ፣ ከሶማሌው፣ ከአዲስ አበቤውና ከጉሙዞ ጋር ብቻ አይደለም ችግር የሚኖረው። በአማራውና በኦሮሞው መካከል በተለይም በሽዋ ዙሪያ ግጭት መነሳቱ የማይቀር ነው። አዳማ፣ ደብረዘይት፣ ዱከም ፣ ፍቼ፣ ደራ፣ አለልቱ፣ ዝዋይ….ባጠቃላይ ሸዋ ልክ እንደ ሞያሌ፣ ሃረር፣ ዴረዳዋ..የይገባኛል ጥያቄ የሚያስነሱ ቦታዎች ናቸው። ከአማራው ጋር። ስለዚህ ሸዋ የኦሮሞ ሆኖ፣ ወይም የአማራ ብቻ ሆኖ መቀጠል አይችልም። ሸዋ የግድ ሕብረብሄራዊ መሆን አለበት።

እንግዲህ የኦሮሞ ጠባብ ብሔረተኝነት፣ የኦነጎችና የነጃዋር የኦሮሞ ፖለቲካ፣ ኦሮሞ ባለፉት ቅርብ ታሪኩ ያላየውን መከራ እያሳዩት ነው። ኦሮሞው ከሁሉም ጋር አብሮ በሰላም የኖረ፣ የተዋለደ ነው። አሁን ግን ከጉሙዙ ጋር፣ ከሶማሌው ጋር፣ ከአዲስ አበቤው ጋር አጋጭተዉታል። እነ ለማ በኦሮሞና በሌላው መካከል ያለውን አጥር ሲሰባበሩ፣ ኦነጎችና እነ ጃዋር ግን የበለጠ እያራራቁትና ከሌላው ጋር ደም እያቃቡት ነው። ስለ ወለጋ ዶ/ር አብይ ሲናገር ሕዝቡ ውሃ ስንጠይቀው ወተት የሚያጠጣ ነው ነበር ያለው።፡ኦሮሞ ደግ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ሌላው አቃፊ፣ ፍጹም ሰላማዊ ህዝብ ነው። ግን ኦነጎችና የጃዋር ቄሮዎች በሚያደርጉት ስራ ኦሮሞው በሌላው እንዲፈራና እንዲጠላ እያደረጉት ነው።

የኦሮሞ ማህበረሰብ መንቃት አለበት። ከአብራኩ፣ ከውስጡ የወጡ ለኦሮሞው አይደለም፣ ለአገር አይደለም፣ ለአህጉር የሚበቁ፣ ከአገር አቀፍ ደረጃ አልፈው በአህጉር ደረጃ ከበሬታ ያገኙ ልጆች አሉት። እነ አቶ ለማ መገርሳ።

ከነዚህ መሪዎቹ ጎን በመቆም ኦሮሞው በሌላው የሚፈራና የሚጠላ ሳይሆን፣ ሌላውን የሚያፈናቅል ሳይሆን፣ ሌላው የሚያነሳ፣ ከሌላው ጋር ሆኖ አገርን የሚገነባ መሆን አለበት።