በነቀምት ከተማ ንብረት አውድሞና ባንኮችን ዘርፎ ከተማዋን ለቆ ከወጣ በሗላ በከተማዋ ዙሪያ ጥቃት እየፈጸመ የሚገኘው የኦነግ ሸኔ ጦር በሸው አከባቢዎችም ጥቃት መፈጸሙ ተሰምቷል። እጅግ ሰቅጣጭ እና አስደንጋጭ ወንጀል በንጹሃን ላይ የሚፈጽመው ኦነግ ሸኔ በወለጋ ብቻ ሳይሆን በአሪስ እና ሸዋ ውስጥም ከፍተኛ የጦር ወንጀል እየሰራ ነው።
በምስል ተደግፎ የደረሰን መረጃ እንደሚጠቁመው በምሥራቅ ሸዋ ዞን ከሞጆ አስከ ዝዋይ በተዘረጋው በአዲሱ የፍጥነት መንገድ ላይ ከሞጆ ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ቆቃ ከተማ አካባቢ ኦነግ ሸኔ በከፈተው ጥቃት 4 ሰው ሲገድል ከ20 በላይ መኪኖችን አቃጥሏል። ይህ መንገድ ከኦሮሚያ፣ከደቡብና ከሲዳማ በርካታ የጭነት መኪኖች የተለያዩ ዕቃዎችን ጭነው ሌሊቱን ሙሉ ወደ አዲስ አበባ ሲመላለሱ የሚያድሩበት ስለሆነ መንግስት ከፍተኛ ጥበቃ ሊያደርግለት ይገባል።
ኦነግ ሸኔ በዚሁ ሳምንት አዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ከሞጆ መቂ መንገድ አንድ ኦባማ ባጃጅ እንደጫነ ከነባጃጇ ሙሉ ለሙሉ ተቃጥሏል። አንድ ሲኖ ከነጫነው እህል ሙሉ ለሙሉ ተቃጥሏል። አንድ ሎቤድ ስካቫተር የጫነ ጋቢናው ብቻ ነዷል። ስካቫተሩ ምንም እንዳልሆነም ተገልጿል። ይህ ጥቃት በዋና ከተማው በቅርብ ሲፈጸም ከመንግስት የተሰተ ምላሽም ይሁም ማስተባበያ የለም።
ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ጀጁ ወረዳ መንበረ ሕይወት ተብሎ በሚጠራው መንደር ውስጥ ጥቅምት 26/2015 ዓም ከምሽቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ በኦነግ ሽኔ አማካኝነት የ8 ወር ህፃን ጨምሮ 3 ሴቶች እና 6 ወንዶችን ገድሏል ። ኦነግ ይህን አሰቃቂ ግድያ ሲፈጽም የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በ300 ሜትር ርቀት ላይ እንደነበርም ተገልጿል። ትእዛዝ አልደረሰንም በሚል የተለመደ ምክንያት እነዚህ ንፁሐን ተገድለዋል። የተገደሉት ወሮ ፍሬሕይወት እውነት፣ ወሮ ሰላም ያሬድ ከነ 8ወር ልጇ፣ አንድ መምህር፣ ሌሎቹ ደግሞ የልማት ሥራ ለመሥራት ከሌላ ሀገር የመጡ ማንነታቸው ያልተወቁ ልጆች እንደሆኑ ነው የተነገረው።
በተጨማሪ በወሊሶ በአሩሲ እና ሸዋ ኩዩ አከባቢዎች ሕዝብን አግቶ ገንዘብ መጠየቁ ተሰምቷል። በወሊሶ ዞን አራት ታዳጊዎች ኦነግ ሸኔ አግቶ ለማልቀቅ ብር ከተየቀ በኋላ የተጠየቀውን ብር ቤተሰብ አዘጋጅቶ ለአጋቾቹ ሊያስረክብ ሲሄድ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ያገኟቸዋል።ሰሜን ሽዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ቀሳውስትን አግቶ በድርድር ገንዘብ ተከፍሎት ሶስቱ ሲለቀቁ ስምንቱ አሁንም በኦነግ ሸኔ እጅ ሆነው እነሱን ለማስለቀቅ ገንዘብ እየተሰባሰበ መሆኑን በምድረ ገነት ቅድስት ልደታ ማርያም የሚገኙ መመናን ይናገራሉ። የኦነግ ሸኔ ጥቃት በዚህ አላበቃም በአርሲ አከባቢ ለቀብር የሄዱ ሰዎችን አግቶ በገንዘብ ለመልቀቅ እየተደራደረ መሆኑ ከመንበረ ሕይወት ከተባለ ስፍራ የደረሰን መረጃ ይገልጻል።