አስኮ አካባቢ የሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖቻችን ጉዳይ አሳስቦኛል – ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ከእስር ቤት

ከወለጋ ተፈናቅለው ሲመጡ የመጀመሪያ ቀን ከተጠለሉበት ወጣት ማዕከል ተባረው ሜዳ ላይ ሳገኛቸው ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኝ ጉዳዩን እዚሁ የፌስቡክ ገፄ ላይ ፅፌ ትበብር ጠየኩ:: Amhara Emergency Fund ወዲያው መልስ ሰጠኝ የ ሶስት ወር ቤት ኪራይ እና ቀለባቸውን ማደሪያቸውን አሟሉላቸው። ከዛም የማስተባበሩን ሀላፊነት እኔ ወስጄ ወዳጆቼን አስቸግር ጀመር። ብዙ መልካም እጆች ተዘረጉ ለጊዜውም ቢሆን የት ይተኛሉ ምን በልተው ያድራሉ የሚለው ስጋቴ ተቀረፈ።

ነገር ግን በቀጣይ በቋሚነት የሚቋቋሙበትና ህፃናቱም ወደ ት/ቤት የሚሄዱበትን መንገድ የማመቻቸትን ስራ በማስተባበር ላይ እያለሁ ለእስር ተዳርግያለሁ።

በመሆኑም ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ የቤት ኪራይና ቀለባቸውን የማግኘታቸው ጉዳይ አሳስቦኛል።

ህፃናቱም ወደ መደበኛ ት/ቤት መሄድ ባይችሉ እንኳን አንዳንድ ቁሳቁሶች ተሟልቶላቸው የቤት ውስጥ ትምህርት እንዲያገኙ ታግዙልኝ ዘንድ በሀገር ውስጥም ሆነ ውጪ የምትገኙ ወገኖቻችን እጠይቃለሁ ።
መዓዛ መሀመድ !

( ልታግዟቸው የወደዳችሁ የሥራ ባልደረባዋን
Misrak Tefera ማናገር እንደምትችሉ የመዓዛ መልዕክት ነው )