" /> በኦህዴዶች ድጋፍ በፈንታሌ፣ ከረዩና ከኢቱ የኦሮሞ ጎሳዎች የመጡ ሽብርተኞች ሕዝብ እያፈናቀሉ ነው – ናኦሜን በጋሻው | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

በኦህዴዶች ድጋፍ በፈንታሌ፣ ከረዩና ከኢቱ የኦሮሞ ጎሳዎች የመጡ ሽብርተኞች ሕዝብ እያፈናቀሉ ነው – ናኦሜን በጋሻው

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ለዉጥ እንዲመጣ ጉልህና ታሪካዊ ሚና የተጫወቱ የሚባሉት አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሞ ክልል ርእስ መስተዳደር ከሆኑ ወደ ሁለት አመት ሊሆናቸው ነው። የለማ ቲም ተብሎ የሚታወቀው፣  አቶ ለማና የትግል አጋሮቻቸው የሆኑ ዶ/ር አብይ አህመድ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ዶር አምባቸው መኮንንና ሌሎችን ያካታተው ቡድን፣ፌዴራል ደረጃ ተጨባጭና የሚታዩ ለውጦች እያመጣ መሆኑም ይታወቃል። የሕሊና እስረኞች ተፈተዋል፤ የፖለኢትካ ምህዳሩ ተከፍቷል፤ የሜዲያ ነጻነት ያለ ገደብ ሆኗል። የአገሩቷን ሃብት የዘረፉና በዜጎች ላይ የሰባአዊ መብት ረገጠ ሲፈጽሙ የነበሩ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው።

ሆኖም በክልል ደረጃ በተለይም በኦሮሞ ክልል፣  በተለይም በክልሉ ለሚኖሩ  በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኦሮሞ ላልሆኑ ኢትይጵያዉያን፣ እንኳን ለውጥ የመጣ እንደውም የባሰበት ሁኔታ እንዳለ ነው ነውሪዎች የሚናገሩት። አቶ ለማ መገርሳ ከክልሉ ስፋት የተነሳም በሚመሩት ደርጅት ኦህዴድ/ኦዴፓ ውስጥ ከተሰገሰጉ ያልተደመሩና አክራሪ አስተሳሰ ካላቸው የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች የተነሳ በክልሉ ሕግን ስርዓትን ማስጠበቅ አስቸጋሪ እየሆነባቸው ነው። ዜጎች መጤ እየተባሉ በተደራጁ አክራሪዎች ዝቻ፣ ማስፈራራት እየደረሰባቸው ሲሆን፣ በአንዳንድ ቦታዎች ሕይወትና እስከማጥፋትና መፈናቀል እስከምፈጠር ድረስ ጥቃቶች የተፈጸሙበት ሁኔታም አለ።

በቅርቡ በምስራ ሸዋ ዞን ፈንታሉእ ወረዳ ፣ አልዴ ቀበሌ የሚኖሩ ነዋሪዎች “ለቃችሁ ውጡ” እንደተባሉና ግድያም እንደተፈጸመ፣ እንደተፈናቀሉም ኢሳይ ዘግቧል። “ቤታችንን ላይ ስማቸውን እየጻፉ ይሄ የኔ ቤት..” ብለው የታጠቁ አክራሪዎች ቤቶቻቸውን እንደወሰዱ ገልጿል። አንድ ኢትዮጵያዊት አባቷ ለወረዳው አስተዳደር ” ባካችሁ ድረስሉን፣ መሳሪያ ይዘው እየዞሩ ነው” በሚሉበት ጊዜ አስተዳዳሪው “ችግር ያለብህ እንደውም አንተ ነህ፣ አርፈህ ተቀመጥ” እንደተባሉና በነጋታው ጠቃት መተው እንደገደሏቸው ተናግራለች። ”

አጎቴን ከዚህ በፊት ገደሉብኝ ፣ አሁን ደግሞ አያቴን ገደሉብኝ። ቤተሰቦቻችን አይምሯችንን በጠበጡት” ስትል ደግሞ አንዲት ሕጻን ታዳጊ ልጅ እያለቀሰች በቀበሌው የደረሰውን ትገልጻለች፡

በፈንታሌ ወረዳ በዜጎች ላይ ችግር እየፈጠሩ ያሉ ከከረዩና ከኢቱ የኦሮሞ ጎሳዎች የመጡ ሽብርተኞች ሲሆኑ የቀበሌውማ የወረዳው የኦሀዴድ/ኦዴፓ አመራሮች ተባባሪ መሆናቸው ኢሳት ዘግቧል።

 

 


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV