መልሶ ማቋቋም የተባለው ፖለቲካዊ ይዘት ያለው እንጂ ያለውን ችግር የሚፈታ አይደለም አቤት የምንልበት አጥተናል

” መልሶ ማቋቋም የተባለው ፖለቲካዊ ይዘት ያለው እንጂ ያለውን ችግር የሚፈታ አይደለም አቤት የምንልበት አጥተናል ” – ተፈናቃዮች

” 72 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ እየተሰራ ሲሆን እስከ ሰኔ ድረስ የወደሙ ቤቶች ለመገንባትና ነዋሪዎችን ወደቀያቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ነው ” – አቶ ባንቄ ኩሜ

በፀጥታ ችግር ሳቢያ በደቡብ ኦሞ ዞን ” አሪ ወረዳ ” የተፈናቀሉ ዜጎች ችግር ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

” ትክክለኛ ፍትህ እንፈልጋለን ”

ህይወታቸውን ሙሉ ደክመው ያፈሩት ንብረታቸው በአንድ ቀን ሙሉ በሙሉ ዶግ አመድ ሆኖባቸው የሰው እጅ ለማየት የተገደዱ ወገኖቻችን ” ፍትህ እንፈልጋለን ” እያሉ ነው።

ሰሞኑን በደቡብ ክልል፤ ደቡብ ኦሞ ዞን ፤ ደቡብ አሪ ወረዳ ከዞን የመዋቅር ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተነሳው የፀጥታ ችግር በርካቶች ንብረታቸው ወድሞ ከገዛ ቤታቸው ተፈናቅለው በየትምህርት ቤቱ እና መንግስት ተቋማት ውስጥ መጠለላቸው ይታወቃል።

ለዘመናት ደክመው ያፈሩት ሀብትና ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሞባቸው በየመጠለያው የሚገኙት ወገኖቻችን መንግስት ጉዳዩን አጣርቶ ትክክለኛ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጥይቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ ለተፈናቃዮች የተለያዩ አካላት ድጋፋቸው ማድረግ የቀጠሉ ሲሆን ከደቡብ ኦሞ ዞን ኮሚኒኬሽን ባገኘነው መረጃ ፤ ባለፉት ቀናት ቀይ መስቀል፣ የዞን ሴቶች መምሪያ፣ የዳሰነች ወረዳ ፣ የቱርሚ ከተማ ድጋፍ ካደረጉት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።