የኢትዮጵያ መንግሥት ከትግራይ ክልል ጋር የገባበትን ጦርነት በሰላም ለመፍታት “እያደረኩት ነው” ያለው ጥረት በህወሓት አመራሮች ተቀባይነት እንዳላገኘ እና በአንፃሩም ህወሓት አማራና አፋር ክልል ውስጥ ትንኮሳ እየፈፀመ መሆኑን ገልፆ በኢትዮጵያ ለዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ትሪሲ ጃኮብሰን ማስረዳቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ አስታወቀ።
በዚህ ጉዳይ ላይ እስካሁን ከትግራይ ክልልም ሆነ ከህወሓት አመራሮች የተባለ ነገር የለም። ሆኖም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሚሰጧቸው ተደጋጋሚ መግለጫዎች ለሰላም ዝግጁ መሆናቸውን፤ የእርዳት እህል ወደ ክልሉ እንዲገባም ይዘዋቸው የነበሩ የአፋር አካባቢዎችን መልቀቃቸውን መግለፃቸው ይዘነጋም። በሌላ በኩል የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ኢትዮጵያ ውስጥ ምግብ ለማቅረብ ችግር እንደሌለና ለተደራሽነቱ የመንግሥት ኃይሎች እንቅፋት መሆናቸውን ተናግረዋል።
In Ethiopia, warehouses are filled with food that’s blocked from getting to millions in need. Progress has been made to increase the trickle of aid previously allowed through—but we need a flood to make up for lost time. pic.twitter.com/oVT7mTrW1s
— Samantha Power (@PowerUSAID) May 11, 2022