በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ዓሳ የማርባት ሥራ ተፈቀደ

በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ዓሳ የማርባት ሥራ ተፈቀደ

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ የዓሳ ማርባት ሥራ መፈቀዱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ። የዓሳ ሀብት ልማት ዕድሎችና ተግዳሮቶችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከዘርፉ ባለድርሻዎች ጋር ማክሰኞ ግንቦት 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ምክክር ያደረገ ሲሆን፣ በዚሁ ወቅትም ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዓሳ ሀብት ያላት ቢሆንም በተገቢው መንገድ ያልተያዘና ጥቅም ላይ ያልዋለ መሆኑ ተገልጿል።