በአዲስ አበባ የሚገኙ አማራ እና የደቡብ ተወላጆች የደህንነት አባላትን ከኔትወርክ ለማውጣት የተደረገው ስብሰባ ከሸፈ

ኦሕዴድ ይህ እርምጃው ካልተሳካ የአማራ ደሕንነቶችን ከመበታተን ጀምሮ ጥቃት እስከ መውሰድ ድረስ ይዘልቃል።

በአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ የተመራ ስብሰባ ላይ የአማራና የደቡብ የደሕንነት አባላት ወኪሎቻችሁን አሳውቁ በሚል የተጠራው ስብሰባ ካለስምምነት መበተኑ ታውቋል። በዚህ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ የተጠሩ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የደሕንነት ሰዎችና በጣም ጥቂት የሚባሉ የደቡብ ክልል ተወላጆች መሆናቸው ታውቋል።  በዋናነት ትኩረት ያደረጉት በከተማዋ ከክፍለከተማ ጀምሮ እስከ ታችኛው እርከን ያሉ እና በአማራ ተወላጆች የተያዙ የደሕንነት ሰንሰሎቶችን መበጣጠስ መሆኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል።

እነዚህ የደሕንነት አባላት የራሷ የደሕንነትና የጸጥታ ተቋም አላት በምትባለው የአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን የውስጥ ምንጮች ይገልጻሉ። 40/ 60 የሚባለው አሰራር ዘርግተናል የሚሉት ገዢዎቹ የከተማው የጸጥታና የፖሊስ ኃይል ከፌዴራሉ የተወጣጣ መሆን አለበት እያሉ ነው። የዚህ ተከታይ ነው የተባለ የደሕንነት አባላቱ ላይ ያተኮረ ስራ በቀንዐ ያደታ እየተሰራ መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች በኝባር ቀደምትነት የዚህ ስራ ዋና አላማ በአማራ ተወላጆች የተያዘውን የደሕንነት መዋቅር መበጣጠስ መሆኑ ታውቋል። በዚህም ምክኛት ነው ለስብሰባ የተጠሩት የአማራ ተወላጆችና ጥቂት የደቡብ ተወላጆች የሆኑት ። በዚህ ስብሰባ ላይ ለደሕንነቱ ሰራተኞች የቀረበው የመጀመሪያ ጥያቄ ወኪሎቻችሁን አሳውቁ የሚል ነው።

ከክፍለከተማ ጀምሮ እስከ ታች ቀበሌ ድረስ የወረዳ ወኪል የቀበሌ ተባባሪ ወኪል የደሕንነት ሰራተኞች መኖራቸው ይታወቃል። የስብሰባው ዋና አላማም እነዚህ ወኪሎችን አሳውቁ የሚል ነው። በደህንነት ስራ ውስጥ አንድ የደሕንነት ሰራተኛ ወኪሉን የማሳወቅ ግዴታ የለበትም። ምክንያቱም እያንዳንዱ የደህንነት ሰራተኛ በወኪሎቹና በተባባሪዎቹ የሚሰራው የደሕንነት ስራ ሚስጥራዊነቱ ተጠብቆ እና የደህንነት ስራዉን አስተማማኝ አድርጎ ለማስኬድ የሚለው አሰራር በመመሪያ ደረጃ ያለ በመሆኑ ነው። እነ ቀንዐ ያደታ ይህንን ጥያቄ ያነሱት  አዲስ እያቋቋሙት ባለው የደህንነት ተቋም ላይ እንቅፋት እንዳይሆንና ያለውን ስጋት ለመቅረፍ ነው ተብሏል። አንድ ሰራተኛ የደህንነት ወኪሎቹን አሳወቀ ማለት ደግሞ ነገሮች ሁሉ አከተሙ እንደማለት ነው ሲሉ አደገኝነቱን የደሕንነት አባላቱ ይገልጻሉ። አንድ የደሕንነት ሰራተኛ የሚያገኘውን ሚስጢር የሚያደርሰው ለአንድ ሰው ወይንም ዘርፍ ብቻ መሆኑ ስራው በምን ያሕል ጥንቃቄ እንደሚሰራ ማሳያ ነው።

የሚሄድበት መንገድ ሁሉ ከሕግ እና ስርዐት ውጪ የሆነ የኦሕዴድ መራሹ አስተዳደር ይህ ስብሰባ ከመካሄዱ በፊት የአዲስ አበባ ደሕንነት ላይ ምክትል ዘርፍ ብለው አዳዲስ ምደባ መፍጠራቸውንና የራሳቸውን ሰው ለመሰግሰግ ዝግጅታቸውን ማተናቀቃቸውን ምንጮቹ ያስቀምጣሉ። ተጨማሪውን ከታችኛው ቪዲዮ ያዳምጡት