ገና ከመግባቷ ወ/ት ብርቱካንን ጭቃ ውስጥ የሚከቱ ጉዳዮች #ግርማ_ካሳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ገና ከመግባቷ ወ/ት ብርቱካንን ጭቃ ውስጥ የሚከቱ ጉዳዮች #ግርማ_ካሳ
የሲዳማ ዞን ምክር ቤት አባላት ነን የተባሉ የራሳችን ክልል ይኑረን በሚል ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ጽፏል። ሕዝብ ዉሳኔ ለማድረግ ማለት ነው። ወ/ት ብርቱካን እነዚህ ክልል እንሁን የሚባሉ ጥያቄዎችን አሁን ማስተናገድ የለባትም ባይ ነኝ።
ስዩም ተሾመ በጥሩ ሁኔታ አስቀምጢታል። ስዩም
” ወ/ሪት ብርቱካን_ሚደክሳ ነገ ጠዋት ቢሮ ስትገባ ከጠረጴዛዋ ላይ ተደርድረው ከሚጠብቋት ደብዳቤዎች ውስጥ የመጀመሪያው ምን ይላል? የሲዳማ ዞን ያቀረበውን የክልልነት ጥያቄ አስመልክቶ “ሕዝበ ውሳኔ (Referendum) እንዲደረግ ስለመጠየቅ” የሚል ነው፡፡ ለዚህ ደብዳቤ ምላሽ በሰጠች ማግስት የወላይታ ዞን የክልልነት ጥያቄ ላይ “ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ስለመጠየቅ” የሚል ደብዳቤ ይመጣል፡፡ ከዚያ በመቀጠል ደግሞ የከፋ_ዞን፣ የሀድያ ዞን፣ የጉራጌ ዞን፣ የስልጤ ዞን፣ የዳውሮ ዞን፣… የራያ_ልዩ_ዞን… ወዘተ የክልልነት ጥያቄ ላይ “ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ስለመጠየቅ” የሚሉ ደብዳቤዎች ይመጣሉ፡፡ ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ስትሰጥ፣ በየክልሉ ሕዝበ ውሳኔ ሲካሄድ፣ ሀገራዊ_ምርጫ ሳይካሄድ በፊት ሀገሪቱ በብሔርና ጎሳ ተሸንሽና…ተሸንሽና ታልቃለች!! ኧረ ፍሬንዶች አረጋጉት!!”
ይላል። እኔም ይሄንን ነው ጭቃ ያልኩት።
– አንደኛ ይሄን የወሰኑ የክልል ምክር ቤቶች በመቶ በመቶ ምርጫ አሸነፍን ያሉ፣ በትክክለኛ መንገድ በሕዝብ ያልተመረጡ ናቸው።
– ሁለተኛ የሲዳማ ዞን የራሳችን ክልል ይሁን ብለው ሕዝብ ዉሳኔ ይሰጥ ብለው እንደጠየቁት፣ የአዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ከሲዳማ ዞን ውጭ የመሆን መብት አላቸውና ፣ ህዝብ ዉሳኔ በአዋሳም የማድረግ ጥያቄ ሊነሳ እንደሚችል መረዳት ያስፈለጋል።
– ሶስተኛ – የሲዳማ ዞን ህየራሱ ክልል ሲሆን የጌዴኦ ዞንን ከተቀረው የደቡብ ክልል ጋር ኩታ ገጠም ባለመሆኑ ይለያል። የሲዳማዎች ዉሳኔም ጌዴዎችንም ይመለከታል። የነርሱን ጉዳይ መጠየቅ አለበት።
– አራተኛ – በሲዳማ ከአዋሳ ጉዳይ ጋር የሚቀራረብ ነው፣ በሲዳማ ክልል ስር መሆን የማይፈልጉ ወረዳዎች አውሳን ጨምሮ ፣ ከሲዳማ ዞን ውጭ የመሆን መብታቸው መከበር አለበት።
በአጠቅላይ ነገሩ በጣም ሲበዛ ውስብስብ ነው። ብርቱካን ሚደቀሳ በነዚህ ጭቃ ጉዳዮች ውስጥ ከወዲሁ ገብታ ራሷን ማጨማለቃ የለባትም። ብዙ አንገብጋቢ ጉዳዮች ከፊቷ ይጠብቃታል።
በኔ እይታ ትኩረቷ ቢሆን ደስ የሚለኝ፡
– ጥቂት ጊዜ ወስዶ ምርጫ ቦርድን መገምገም
– አባላት የሌⶀቸው፣ ጽ/ቤት የሌሏቸው፣ ጠቅላላ ጉባዬ አድርገው የማያውቁ፣ የምርጫ ቦርድ ሰርተፊኬት ያላቸውን በመሰረዝ የተቃዋሚዎችን ቁጠር እንድቀንስ ማድረግ።
– ተቃዋሚዎችና ተቃዋሚዎችን በአንድ ላይ በማምጣት፣ በጋራ ሌሎች የቢርድ አባላት በመምረጥ፣ ቦርዱን ማጠናከር።
– በየወረዳው፣ ገለልተኛ፣ ብቃትት ያላቸውን የምርጫ ቦርድ ተወካዮችና ጽ/ቤቶችን ማዋቀር
ይሄን ለማድረግ ቢያንስ ወ/ት ብርቱካን ስድስት ወራት ይፈጅባታል። እስከዚያው ድረስ ምንም አይነት ምርጫ ማድረግ አስፈላጊ አይደለም።