የሕወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስካልተወገደ ድረስ የኢትዮጵያ ስጋት መሆኑ አይቀርም መቼም ቢሆን በድል ሰክረን አንተኛም – ሜጀር ጄነራል ሙሉዓለም አድማሱ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ምክትል

May be an image of 1 person, military uniform and text that says 'እፕድ Ethiopian Press Agency Gebabo Gebre'የሕወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስካልተወገደ ድረስ የኢትዮጵያ ስጋት መሆኑ ስለማይቀር መቼም ቢሆን በድል ሰክረን አንተኛም ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሙሉዓለም አድማሱ ገለጹ።

ሜጀር ጄነራል ሙሉዓለም አድማሱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስካልተወገደ ድረስ የኢትዮጵያ ስጋት መሆኑ አይቀርም። የሽብር ቡድኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ስለማይተኛ እኛም መቼም ቢሆን በድል ሰክረን አንተኛም ብለዋል።

ጦርነት ለሽብር ቡድኑ የመኖርና ያለመኖሩ ጉዳይ ስለሆነ ከዚህ በኋላም ቢሆን ወረራ ለማካሄድ ሊሞክር ይችላል ያሉት ሜጀር ጄነራል ሙሉዓለም፤ የሽብር ቡድኑ በአሁኑ ጊዜ በሰው ኃይል፣ በትጥቅና በመሳሪያ ተዳክሟል፤የሞራል ውድቀትም ደርሶበታል ነው ያሉት።

በተቃራኒው በወገን ኃይል የድል ባለቤት በመሆኑ የበለጠ መነሳሳትና ወኔ ተፈጥሯል፣በቂ ዝግጅትም ተደርጓል፤ ከአሁን በኋላ የሽብር ቡድኑ ከስህተቱ ሳይማር ቀርቶ ወደ አፋርም ሆነ አማራ ክልሎች እስፋፋለሁ ቢልም እሳት ይጠብቀዋል ብለዋል።

አሸባሪው ሕወሓት ኢትዮጵያን ለመበታተንና መንግሥትን ለመጣል ዕቅድ ይዞ ያለ የሌለ ኃይሉንና የቀበረውን መሳሪያ አሰባስቦ አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ያደረገው መፍጨርጨር መና እንደቀረና በጀግናው መከላከያ ሠራዊትና በጥምር የጸጥታ ኃይሎች ተቀጥቅጦና ድባቅ ተመትቶ ወደ ኋላ መመለሱን መግለፃቸውን የዘገበው ኢፕድ ነው።