በኦሮሞ ክልል ሽብርና የመንግስት ዝምታ #ግርማ_ካሳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ወደ ኢሉባቡር በጉኖ በደኖ ዞን ደደሳ ወረዳ ዜጎች እየተፈናቀሉ ነው። በተለይም አማራዎች ከጥቅምት 10 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ ቤታቸው ሲቃጠል እንደሰነበተና ዛሬ አዳሩን እሩምታ ሲተኮስባቸው እንዳደረ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፍራው ሸግቧል።

እንደ ጋዜጠኛው ዘገባ በተለይም በጨረቻ በቡርቃ ጃላላና በመደሚስት በ ሁኔታዎች የከፋ ደረጃ ላይ ነው ያሉት። ቤት ንብረቶቻቸው ተቃጥለው ደዮ በምትባል ንዑስ ፖሊስ ጣብያ አካባቢ ሜዳ ላይ ተበትነዋል።

ይህ አይነት ተመሳሳይ ግፍና በደለ በሌሎች ማህበረሰባት ላይ ሲወሰድ በአቶ ለማ መገርሳ የሚመራው አመራር የቃላት ማስጠንቀቂያ ከመስጠትና መግለጫ ከማወጣጥ ያለፈ ምንም አይነት ተግባራዊ እርምጃዎች መዉሰድ አልቻለም። ያም የሆነበት ትልቁ ምክንያት የኦሮሞ ክልል በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ ከአዳማ ራቅ ባሉ እንደ ወለጋ፣ ሃረር፣ ኢሊባቡር ባሉ አካባቢዎች ሕግን የማስከበር አቅም ስለሌለው ነው።ሌላው ምክንያት አቶ ለማ መገርሳ በሚመሩት ኦዴፓ ውስጥ በዞንና በወረዳ ያሉ አመራሮች ያልተደመሩ፣ የጥላቻ አመለካከት ያላቸው መሆናቸው ብቻ ሳይሆን እነ አቶ ለማ መገርሳን ሳይሆን ለሌሎች ጽንፈኛ አካላት የሚታዘዙ መሆናቸው ነው።

አሁንም ዶ/ር አብይ ከዝምታ ወጥተው በነዚህ አካባቢዎች የፌዴራል ሰራዊትን እንዲያሰማሩና ከሕገ ወጥ የሆኑ ኦ እጎችንና አልቄሮዎች አንድ እኒሉልን በአጽንዎት እጠይቃለሁ። የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛኝ ናቸው። ለመስራቅ እዝና ለምእራብ እዝ አዛዦች ሁለት መስመር ትእዛዝ መስጠት ብቻ ነው የሚያስፈልጋቸው። የመከላከያ ሰራዊት በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁሉንም ማረጋጋት ይችላል። ትእግስትም ገደብ አለው።