በሸዋ የህወሓት ኃይል በኢትዮጵያ ጦር ተከብቧል፤ በዋግ ኽምራ ዞንም ዉጊያ ቀጥሏል !

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና ዋግኽምራ ዞኖች ጦርነቶች መቀጠላቸውን የሁለቱ ዞኖች አስተዳዳሪዎች በየፊናቸዉ አስታዉቀዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ ታደሰ ገ/ፃዲቅ ለDW ባሕርዳሩ ወኪል እንደነገሩት በአካባቢዉ የሚገኘዉ የህወሓት ኃይል በኢትዮጵያ ጦር ተከብቧል።በዋግ ኽምራ ዞንም ዉጊያ መቀጠሉን የዞኑ ባለስልጣናት አስታወቀዋል።የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ ተስፋ ዬ ገብሬ እንዳሉት በተለይ ቆዝባ በተባለ አካባቢ ዉጊያዉ ተጠናክሮ ቀጥሏል።የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ግንባር መዝመት ለጦሩና ለደጀኑ ሕዝብ ተጨማሪ ኃይል መሆኑንም ባለሥልጣናቱ አስታዉቀዋል።