ደሴ፣ኮምቦልቻ፣ ሃይቅና ቢስቲማ – #ግርማካሳ

ደሴና ኮምቦልቻ በቅርብ ርቀት ላይ ያሉ ከተሞች ናቸው።ደሴ ተራራ ላይ ከፍ ብላ፣ ሸዋ ሮቢት ደግሞ በቆላው ወረድ ብላ ያሉ ከተሞች።
ደሴ ከፍተኛ ዉጊያ ከተደረገና፣ በተለይም በቦሩሜዳ እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሕወሃት ታጣቂዎች ከተቀጠፉ በኋላ፣ አስቀድሞ “ተፈናቃዮች ናቸው” በሚል በደሴ ከተማ የሰረጉ ወያኔዎች፣ የወገንን ጦር ከጀርባ በመውጋታቸው ፣ ያንንም ተከትሎ በተፈጠረው ክፍተት፣ ወያኔ ደሴን መያዟ ይታወሳል። የመሬቱ አቀማመጥ ከላይ ወደ ታች በመሆኑም ኮምቦልቻንም መያዝ አስቸጋሪ አልነበረም።
ወያኔዎች ከኦነግ ጋር ጥምረት በመፍጠራቸው፣ ኦነጎች ለሁለት አመታት ያለምንም ችግር ሲንቀሳቀሱበት የነበረውንና በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኘው የኦሮሞ ሄረሰብ ዞን : ለወያኔዎች ደጀን ዞን በመሆኑ፣ በሰዓታት ውስጥ ባቲን ይዘው አፋር ድንበር፣ ኬሚሴን ይዘው ሰሜን ሸዋ ድንበር ደረሱ::
ሆኖም ግን በአፋር ግንባሮች ሆነ በስሜን ሸዋ ግንባሮች እንዳሰቡትና እንደጠበቁት እልሄደላቸው:: የጅቡቲ አዲስ አበባን መስመር መያዝም ሆነ ሸገር መግባት አልቻሉም።
እንደውም ባለፉት ሁለት ቀናት ከደቡብና ከምእራብ የወገን ጦር ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ሃይቅና ቢስቲማ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ነጻ ሊወጡ እንደሚችሉ የሚያሳዩ ምልክቶች እያየን ነው።
1ኛ – የወገን ጦር ከሃይቅ ከተማ በስተምስራቅ የምትገኝዋን ቢስቲማ ከተማ ለመያዝ እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ ሰምቻለሁ፡፡ እዚያ አካባቢ ኔትዎርክ ብዙ ስለሌለ እንጂ፣ ይሄን ጊዜ ቢስቲማም በወገን ስር ልትሆንም ትችላለች፡፡ ከቢስቲማ ጎን ያለችው የሃይቅ ከተማም የወገን ጦር ገና ያልገባባት ቢሆንም ወያኔዎች ብዙ የማይታይባት ባዶ ከተማ መሆኗን የሚገልጹ መረጃዎች አሉ፡፡ በቢስቲማ ነገሮች ከጠሩ በቀላሉ ሃይቅም ገቢ መደረጓ አይቀሬ እንደሚሆን ነው የሚታሰበው።
2ኛ ከምእራብ ወሎ የተንቀሳቀሰው አርበኛ ዘመነ ካሴ የሚመራው የፋኖ ጦር፣ በርካታ የምእራብ ወሎ ገጠራማ አካባቢዎችን በማጥራት ወደ ደሴ ከተማ
እየገሰገሰ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
በደሴ ውስጥና በደሴ ዙሪያ ሽምቅ ውጊያ እያደረጉ ካሉ የወሎ ፋኖዎችና ሚሊሺያዎች ጋር በመሆን ሙሉ ሙሉ ወያኔዎችን ከደሴና ከደሴ አካባቢ የመልቀም ስራ ይሰራል ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡
3ኛ ወያኔዎችና ኦነጎች፣ የአፋር ግንባር ማዘዣቸውን በኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን ባቲ አድርገው፣ ሚሌን ለመያዝ በካሳጊታና ቡርቃ በኩል ከ15 ቀናት በላይ፣ እጅግ በጣም ከፍተኛና በርካታ ዉጊያዎች አድርገዋል። በባቲ አካባቢ ያሉ ተራራማ አካባቢዎች ላይ ምሽጎች በመስራት፣ ከባባድ መሳሪያዎችን በመትከል፣ የከባድ መሳሪያዎች ድብደብ ሲያደርጉ ነበር።
ነገር ግን ከ15 ሺህ በላይ ታጣቂዎች ከመገበር ውጭ ያገኙት አንዲት ነገር የለም። የትግራይ ሜዲያ ሃዉሶች፣ እነ ስታሊን ገብረስላሴ ሚሌ ገባን ብለው ሲቀደዱ የነበረ ቢሆንም፣ ሚሌ መድረስ አልቻሉም።
የወገን ጦር ማጥቃት እንዲጀመር ትእዛዝ ከተሰጠ በኋላ በመከላከል ላይ ያተኮረው የአፋር ጀግኖችና መከላከያን ያካተተው የወገን ጦር፣ በባቲ አካባቢ ያሉ ምሽጎችን በመደርመስ የወያኔ/ኦነግ የአፋር ግንባር ማዘዣ የነበረችውን የባቲ ከተማ ሊቆጣጠር ችሏል፡፡
ያ ብቻ አይደለም የወገን ጦር ገፍቶ በመሄድ በኮምቦቻልና ባቲ መካከል ፣ ከኮምቦልቻ የ30 ኪሎሜትር ወይንም 45 ርቀት ላይ ብቻ ያለችውን ገብራን ነጻ በማውጣት ወደ ኮምቦልቻ እየገሰገሰ ነው፡፡
4ኛ ሌላዋ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ከተማ፣ ከሚሴ በስሜን ሸዋ ግንባር የተሰማራው የኦነግና የሕወሃት ጦር ማዘዣ ከተማ ናት፡፡ የወገን ጦር በከሚሴና በኮምቦልቻ መካከል ያለችውን የሃርቡ ከተማን ቆርጦ በመቆጣጠር ከሚሴን ጨምሮ ወደ ሸዋ የተሰማራው የወያኔ/ኦነግ ጦር ሙሉ ለሙሉ እንዲቆረጥ አድርጓል። ከወሎ ወደ ስሜን ሸዋ የተሰማሩ የወያኔ ታጣቂዎች ከመሞት ወይንም እጅ ከመስጠት ውጭ ሌላ አማራጭ አይኖራቸውም።
ሃርቡ ከኮምቦቻል 22 ኪሎሚተር ወይም በ30 ደቂቃ ረቀት ላይ ያለች ከተማ ናት፡፡ የወገን ጦርም ከሃርቡ ወደ ኮምቦልቻ እየገሰገሰ ነው፡፡
ሃይቅ፣ ደሴ፣ ቢስቲማንና ኮምቦልቻ ለመያዝ ወያኔ እጅግ በጣም ብዙ ሰው ነው የገበረችው፡፡ ከባድ ዋጋ ነው የከፈለችው፡፡
“ሕዝብን ማሸነፍ አትችሉም፣ የትም አትደርሱም፣ ይልቅ ምስኪን የትግራይን ወጣት አታስጨርሱ፣ ያሉ የፖለቲካ ልዩነቶች በውይይት መፍታት ይችላል፣ ወራችሁ ከያዛቹኋቸው የኣማራና የአፍር ክልል ውጡና ለድርድር ተዘጋጁ” ብለን ብዙ ስንማጻናቸው ነበር፡፡ ይኸው አሁን ሳይወዱ በግድ እጅ በመስጠት ወይንም ወደዚያኛው አለም በመሄድ ወረው ከያዙት አንድ በአንድ እየለቀቁ ነው፡፡ በጣም ያሳዝናል። እንደዚያ መሆን አልነበረበትም። ግን እነርሱ ለመገደል፣ ለመዝረፍ፣ ለማጥፋት ሲመጡ እነርሱን መመከትና ማስቆም የሕልውና ጉዳይ ስለሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም።
የተጀመረው የማጥቃት ዘመቻ በቶሎ በድል የሚጠናቀቅበት፣ በትግራይ ሕዝብና በትግራይ ወጣቶች ሕይወት ቁማር እየተጫወቱ ያሉ ወንጀለኞች፣ የሕወሃት መሪዎች የሚያዙበት ወይንም የሚወገዱበት እና በወያኔና ኦነግ የተፈናቀሉ ወደ ቅያቸው የሚመለሱበት ጊዘ ይፋጠን ዘንድ፣ ሁላችንም የድርሻችንን ለማድረግ መረባረብ ጊዜ የሚጠይቀው አገራዊ ሃላፊነትና ግዴታ ነው።