#ጤናማቃላት ( #KeepWordSafe ) የተሰኘ የማህበራዊ ገጾች ንቅናቄ ይፋ ተደረገ

በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ የሚለጠፉ ሀሳቦች ሰብአዊ መብቶችን ያከበሩ እንዲሆኑ ማድረግን ዓላማ ያደረገ ‘ሃሽታግ’ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ይፋ ተደርጓል።

#ጤናማቃላት (#KeepWordSafe) በግለሰቦች፣ በማህበረሰብ እና በተቋማት ደረጃ የሚደረጉ ዉይይቶችና ክርክሮች ከማንነት ይልቅ በሃሳብ ላይ እንዲያጠነጥኑ እንዲሁም ጥላቻና ግጭት እንዳያስነሱ ለማድረግ እንደሚያግዙ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በድረ-ገጹ ገልጿል።

#ጤናማቃላት እ.ኤ.አ. በ2021 ዓመት በሚታሰቡ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ቀናት ላይ በዋነኛነት ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል።
ህዳር 11 ቀን 2014 ታስቦ በዋለው ዓለም አቀፍ የህጻናት ቀን በይፋ የተጀመረው #ጤናማቃላት በእዚሁ ዓመት በሚታሰቡት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የማስወገድ ቀን፣ የአካል ጉዳተኞች ቀን፣ የሰብአዊ መብቶች ቀን እንዲሁም የፍልሰተኞች ቀንን ጨምሮ ለ9 መድረኮች ሰፊ ጥቅም ላይ ይውላሉ ተብሏል።

ኮሚሽኑ አክሎ እንደገለጸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚተላለፉ ሃሳቦች ጤናማ እና ሰብአዊ መብትን ያከበሩ እንዲሆኑ የሚመኝ ማንኛውም ግለሰብ #ጤናማቃላትን መጠቀም እንደሚችል አስታውቋል።