ከነገ ጀምሮ ውጊያው ሁሉም የፀጥታ አካላት በቅንጅት ወደተለየ እርምጃ እንዲሸጋገሩ ትዕዛዝ ተሰጠ

የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ እንደተወያየ ፓርቲው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል።

ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ማስቀመጡን ፓርቲው አክሎ የገለጸ ሲሆን፣ ኮሚቴው በዝርዝር በየትኞቹ ጉዳዮች ላይ እንደተወያየ እና ምን ውሳኔዎችን እንዳሳለፈ ግን ፓርቲው አላብራራም። ሆኖም ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ማምሻውን መግለጫ ሊያወጣ እንደሚችል ታውቋል።

ኮሚቴው በዛሬው እለት ባካሄደው ስብሰባ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክሮ የተለያዩ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥም ስብሰባውን ማጠናቀቁን ከብልጽግና ፓርቲ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

” ከፓርቲው ፕሬዝዳንት (የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ) ጀምሮ ወደ ግንባር ሄደን እኛ መስእዋት ሆነን ኢትዮጵያን ለማዳን ወስነናል ” – ዶ/ር አለሙ ስሜ

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክሮ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት በውስጥም በውጭም የተከፈተባት ጥቃት የተቀናጀ መሆኑን ገልጾ፤ ሽብረተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህወሓትና ግብረአበሮቹ በኢትዮጵያ እስካሁን ለደረሰው ጥፋት ተጠያቂ ናቸው፤ ተጠያቂነቱም ይረጋገጣል ብሏል።

ውጊያው አሁን ካለው የበለጠ ኪሳራ እንዳያደርስ ከነገ ጀምሮ ሁሉም የፀጥታ አካላት ወደተለየ እርምጃ እንደሚሸጋገሩ ተገልጿል።

ዶ/ር አብርሃም በላይ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ፥ መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፀጥታ አካላት በቅንጅት ተዘጋጅተው ወደተለየ እርምጃ ይገባሉ ይህ ምን ጥያቄ የለውም፤ ለውጥ ይኖራል ” ብለዋል።

በተጨማሪ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በስብሰባው ላይ ከዚህ በኃላ ሁሉም አመራር በየጦር ግንባር እየተገኘ የህልውና አደጋውን ለመቀልበስ ከፊት ሆኖ እንደሚሰለፍ አሳውቋል።

ዶ/ር አለሙ ስሜ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል፥ ” የብልፅግና ስራ አስፈፃሚ ከፓርቲያችን ፕሬዜዳንት (ከሀገሪቱ ጠ/ሚኒስትር) ጀምሮ ወደ ግንባር መግባት እንዳለብን በእርግጥ ሌሎች ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ የተወሰነ የልማቱን ስራ ፣ የዲፕሎማሲውን ስራ፣ ከቢሮ የሚሰራውን ስራ እንድንሰራ ሌሎች ከዚህ ውስጭ ያለን ከፓርቲያችን ፕሬዜዳንት ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ጀምሮ ወደ ግንባር ሄደን እኛ መስእዋት ሆነን ኢትዮጵያን ለማዳን ወስነናል፤ ይሄንንም በተግባር ከነገ ጀምሮ በመንቀሳቀስ የምናሳየው ይሆናል ” ብለዋል።