በታጣቂዎች የተከበቡት የአሰቦት ገዳም መነኰሳት የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው፤የወረዳው አስተዳዳሪ “ለቃችሁ ውጡ” በማለት እገዛ አላደረገም

  ከጥቅምት 7 ጀምሮ በየምሽቱ ከታጣቂዎቹ ጋራ የተኩስ ልውውጥ በማድረግ ላይ ናቸው፤ ታጣቂዎቹ፣“የኦነግ ወታደሮች ነን”ቢሉም ተከፋይ ሁከተኞች ሊኾኑ እንደሚችሉ ተነግሯል፤ የወረዳው አስተዳደሪ፣ ጥበቃ እንዲያደርግላቸው በዞኑ የተላለፈለትን ትእዛዝ አልፈጸመም፤ በሶማሌ ክልል ወሰን በኩል የመከላከያ ድጋፍ ቢጠየቅም ኦሮሚያ መፍቀድ አለበት፤ተብሏል፤ አንዱ በሌላው ሲያመካኝ፣ የግንቦት 1984 ዐይነቱ ወረራና እልቂት እንዳይደገም አስግቷል፤ በስብሰባ ላይ ያለው ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ በአስቸኳይ የኦሮሚያን …