በኢትዮጵያ በሁለት ቀናት ውስጥ ከ70 በላይ ሰዎች በኮቪድ መሞታቸው ተመዘገበ

በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ቀናት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ከ70 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተመዘገበ። ከጤና ሚንስቴር እና ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ማክሰኛ መስከረም 4/2014 ዓ.ም. ከወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የ34 ሰው ሕይወት አልፏል። ሰኞ መስከረም 3/2014 ዓ.ም. ደግሞ ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የ38 ሰዎች ሕይወት አልፎ፤ በሁለቱ ቀ…