በዛሪማ ድብባህር ሊማሊሞ ደባርቅን ለመቁረጥ ውጊያ የከፈተውን የሕወሓት ቡድን ተደምስሶ አከባቢው ነጻ ወጣ !

May be an image of 8 people, people standing, military uniform and outdoorsበማይጠብሪ ግንባር በዛሪማ ድብባህር ሊማሊሞ ደባርቅን ለመቁረጥ ውጊያ የከፈተውን የሽብር ቡድን በመደምሰስ አካባቢውን ነፃ ማድረግ መቻሉ ተገለፀ። በዳባት ውቅን አቅጣጫ የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስና ደባርቅን ተቆጣጥሮ ወደ ጎንደር ለመግባት ያለመው የሽብርተኛው ቡድን በብናሜዳ፣ ቦዛ፣ ጭና የነበረውን የቀኙን ክንፍ የውጊያ አቅጣጫ ለማዛባት ቢጥርም መደምሰሱን የወገን ጦር መሪዎች ገልፀዋል።
የወገንን ፈጣን የማጥቃት እንቅስቃሴ ለመግታት የዛሪማ ድልድይን በፈንጂ ለማፍረስ ብዙ ቢጥርም በደረሰበት ጥቃት መሽመድመዱን የተናገሩት ከፍተኛ አመራሩ፤ ጠላት መልሶ እንዳይቋቋም የሚያደርግ ምት በማሳረፍ ዛሪማና አካባቢው በማይጠብሪ ግንባር በተሰለፈው የመከላከያ ሰራዊታችንና የወገን የፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ይገኛል ነው ያሉት።
ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለተገኘው ድል በማይጠብሪ ግንባር የተሰለፈው የወገን ኃይል ጥምረት የላቀ እንደነበር የተናገሩት የጦር መሪው፤ አሁንም ዙሪያ መለስ የውጊያ ቁመናን በማሟላት ለቀጣይ ግዳጅ በሙሉ አቋም ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።
የሽብር ቡድኑ በዛሪማ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ተቋማትን እና የሕዝብን ንብረት ዘርፏል።
ሆኖም በጠላት ላይ በተወሰደ እርምጃ አሁን ላይ ማኅበረሰቡ ወደ መደበኛ ኑሮው በመመለስ ላይ መሆኑ ተገልጿል።
ምንጭ ዋልታ
May be an image of outdoors