ሱዳን በህዳሴ ግድቡ ሙሌትና አሰራሮች ላይ አስገዳጅ ስምምነት እንዲደረግ ጥሪዋን አላቆምም አለች

Sudan will spare no effort to reach binding agreement on GERD : Hamdok

ሱዳን በህዳሴ ግድቡ ላይ አስገዳጅ ስምምነት ላይ ለመድረስ አሁንም ጥረቴን አላቆምም አለች

ሱዳን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ቢጠናቀቅም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሌትና አሰራሮች ላይ ህጋዊ አስገዳጅ ስምምነት እንዲደረግ ጥሪዋን እንደምትቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ አስታውቀዋል ፡፡

Sudan will continue to call for a legally binding agreement on the filling and operation of the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GRED) despite the completion of the second filling, said Prime Minister Hamdok on Tuesday. On 19 July, Ethiopia has completed the second year filling of the GERD reservoir by impounding 13.5 bcm. In a speech broadcast to the nation on the occasion of Eid Al-Adha, Hamdok stressed that the dam issue remains at the top of the priorities of his government.

ሃምዶክ የኢድ አል-አድሃ በዓልን አስመልክቶ ለህዝቡ ባስተላለፉት ንግግር የግድቡ ጉዳይ በመንግሥታቸው ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ሆኖ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል፡፡

የሱዳንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ምንም ነገር እናደርጋለን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ ሱዳን ትሪቡን ዘገባ፡፡

ግድቡ በአለም አቀፍ ህግ አስገዳጅ ስምምነት ሊሞላ ወይም ሊሰራ እንደሚገባው የካርቱም ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡

“Despite the announcement by the Ethiopian government of the completion of the second filling in continuation of its unilateral actions, we continue to call for refraining from unilateralism and conclude a legally binding agreement under the international law,” said Hamdok. “We will spare no effort to achieve this goal to preserve Sudan’s national interests,” he further stressed.

ኢትዮጵያ ሦስቱ አገሮችን የሚጠቅመውን ግድብ ለማሳካት ሱዳን እና ግብፅ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርባለች፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ማክሰኞ ዕለት ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዑክ ጋር በነበራቸው ቆይታ በመጋቢት ወር 2019 በሶስቱ ሀገራት በተፈረሙ መርሆዎች መሠረት በክረምት ወቅት ሁለተኛው ሙሌት መከናወኑን ተናግረዋል ፡፡