የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈጸመ


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ የቀብር ስነ-ስርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በተገኙበት ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።
ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅጥር ግቢ /ማዘጋጃ ቤት/ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አፈጉባኤ ወ/ሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ወዳጅ ዘመድ እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ተከናውኗል።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በሽኝት ስነስርዓቱ እንዳስታወቁት ከንቲባ ዘውዴ በስራ ዘመናቸው የሀገራችን እና የከተማችንን የስልጣኔ የከተሜነት ጉዞ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ህያው መሆኑን ገልጸዋል ።
ከንቲባ ዘውዴ የከተማዋ ነዋሪዎች በማህበር እንዲደራጁ ከማድረግ ባለፈ በከተማ ፕላን ፣የአዲስ አበባ ሙዚየም እና ሌሎች ከ9 በላይ የህዝብ መናፈሻዎችን በማሰራት ዘመን ተሻጋሪ ስራ መስራታቸውን ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መናገራዠውን የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ዘግቧል።
ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ በ1973 ዓ.ም በተደረገው 3ኛ ዙር የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ማኅበራት ምርጫ ከንቲባ በመሆን ተመርጠው ከ1973 እስከ 1981 ዓ.ም ድረስ በከንቲባነት አገልግለዋል።
ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ ከአባታቸው ከባሻ ተክሉ አመኑና ከእናታቸው ከወይዘሮ አስካለ ደገፉ በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት በሃረር ዙሪያ አውራጃ በኤጀርሳ ጎሮ ወረዳ ገንደጋራ በሚባል አካባቢ መጋቢት 7 ቀን 1928 ዓ.ም ተወልደዋል።