" /> ለግንቦት 7፣ ኦነግ፣ OMN እና ኢሳት አመራሮችና አፈቀላጤዎች አጭር መልእክት አለኝ (አባዊርቱ) | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ለግንቦት 7፣ ኦነግ፣ OMN እና ኢሳት አመራሮችና አፈቀላጤዎች አጭር መልእክት አለኝ (አባዊርቱ)

ከአባዊርቱ

ሀሳባችሁ በጭራሽ ሊገባኝ አልቻለም:: በደፈናው ግን የበላችሁበትን ወጪት ሰባሪዎች ናችሁ:: እኒህ ቅን መሪ እውራን በበዙበት ሀገር በፈጣሪ ሀይል ብቅ ብለው ለአገር በጋራ እንተልም ባሉና ዘንባባ አንጥፈው በተቀበሉ ያውም ሹማምንት ኤርፖርትና በየኬላው እየላኩ አክብረው ትልቅ ትንሽ ሳይሉ አስቤዛና ማረፊያ ቤት ሳይቀር በተቀበሉ እጉያቸው ስር ሆናችሁ እንደምስጥ ትሰረስሩዋቸው ጀመር? ለናንተ ስልጣን ብላችሁ መንበሩ ሳይረጋ እንዲህ ባደባባይ ታሳፍሩን? ምን የሚሉት ጎራ ለይቶ ሽኩቻ ነው? ድንቄም ተፎካካሪዎች:: ተቃርኖዎችም ሲያንሳችሁ ነው:: ምኑ ተያዘና ነው እንዲህ ከወዲሁ የሚያወራጫችሁ? በናንተ መሻኮት ደሀው በኑሮ መዛባት መሞቱ ሳያንስ በቀዳዳ ጅቦች እያስገባችሁ ቤታችንን እንዲህ ታሳምሱት? እናንተ እዛ ምድር ሳትረግጡ በፊት ሰው እየፈነጠዘ አልነበረም? ምን አይነት ጉዶች ናችሁ በፈጣሪ? ትምህርትና ማገናዘብ እንዲህ ነው? የናንተን መሻኮትን ተጠቅመው የፅልመት ሀይሎቹ ከጀርባ ትከሻችሁ ስር መድረሳቸውን ልብ ብላችሁዋል? ወይስ ግድ አይሰጣችሁ ይሆን? ስው ታዘባችሁ እኛም አፈርንባችሁ:: አሁን በቅርብ አልነበረም እንዴ እዚሁ ውጭ አንድ ገበታ ቀርባችሁ ስታወያዩን የነበረው? ለአገር ወገን ስትሉም አልነበረም እንዴ? ምን ታረጉ:: እራሱን ዝቅ አድርጎ ጭቃ በጁ ነክቶ ቤት መሰረት የሚጥል መሪ መጣባችሁና እንደመሸባችሁ ስታዩት መባላቱን ተያያዛችሁ:: እንግዲህ ከምኑም የሌለሁ ታዛቢ መርዶ ላርዳችሁ!!

አቢይና እነ ኦቦ ለማ ብሎም ደመቀና ገዱ ዛሬም ነገም በትንሹ እስከ ሁለት ምርጫ ያስተዳድራሉ ያቺን ምስኪን ሀገር:: ለምን? የቅንነት ፀጋ ተላብሰዋልና:: እናንት በተለይ እድሜአችሁ የገፋው ሀላፊ ተብዬዎች እስቲ በየቡድን ላርዳችሁ: እንደገና::

ግንቦቴዎች:

ዶር ብርሀኑ የኢኮኖሚክስ ማህበርን ተቀላቅለህ ወይም ጥሩ የከንሰልቲንግ ቢሮ ከፍተህ አቢይን እርዳቸው:: ምስጉን ምሁር ነህ:: ውጤቱም ያማረ ይሆናል በጥቂት ጊዜ ውስጥ:: አመራር እኮ በሙያም ይቻላል:: የግድ የፖለቲካ ካባ ማጥለቅ አኖርብህም:: እዚህ ብዙም ስለኖርክ ናላህን ያዞሩታል ፖለቲካው ውስጥ ብትገባ አሁን:: የብሄር ፖለቲካ is here to stay. Please consider this seriously.

አንዲ በቃህ የኔ
ወንድም:: እነዛን ብርቅዬ ልጆችህን ተመልሰህ በወግ አሳድግ:: በስተርጅና ወልደህ ገና ጠረንህን በደንብ ሳያውቁ እየመሸ ነውና:: ከፋሚሊ በላይ አገር ትርጉም የለውም:: የኢሀፓ ዘመን አገር ወይም ሞት ላይ አይደለንም:: ባለፈው ያየህው መከራ ይበቃል:: አይይ ፖለቲካው አይቅርብኝ ከሆነ ግን አንተም የ intergovernmental affairs አይነት አቁምና በኤርትራ ና ኢትዮጵያ መሀል ጥሩ ድልድይ ትፈጥራለህ:: እንደኔ ግን እነዛ ብርቅዬ ልጆች ጋ ተመለስ::

ኦነጎች

የናንተው ግራ ይገባኛል:: መቼስ ኦሮሞን የመሰለ ግንድ አሁንም እንገነጥላለን እንደማትሉ በማመን እስቲ ከዶር መረራ ተቀራረቡ:: ታረቁ:: በአባገዳዎች የሚመራ ታላቅ ጉባኤ ጥሩና አንድ ወይም ከፍ ካለ ሁለት አቅጣጫ ያዙ:: ድካማችሁ ለወገናችን ከሆነ:: ይህን የአቢይን ትውልደ ኦሮሞ ለመከፋፈልና ለመቀራመት አስባችሁ አላስፈላጊ ክፍፍልን በይፋም ይሁን በስውር አካሄዳችሁ አላማረኝም:: ቄሮ ማ ምን ላይ ተጥዶ ድል እንዳስመጣ ያውቃል:: የአቢይን ትውልድ ለመናድ ወይም ለማሸሽ የምታረጉት ሁሉ ውለታቢስነት ነው:: ምን አረጋችሁ ግቡና አብረን እንስራ ከማለት? በእድሜው የገፋችሁ ሌላ ስራ ፈልጉ:: ለታደለው ማስተማርም ልዩ ፀጋ ነውና:: ወጣቶች ካላችሁ እኔ እናንተን ብሆን ከለማ እጠጋለሁ ያውም አገራዊ ፓርቲ በፈጠሩ ማግስት::

ጃዋርና ኢሳቶች!

አደብ ግዙ:: አስተውሉ:: ብዙ ወጣቶች ሆምዎርካቸውን ትተው እናንተ ላይ ተጥደው ነው የሚውሉትና የሚያድሩት:: ቀላሉን ነገር አካብዳችሁ አታሰቃዩን:: ከባዱን እንኩዋ ቢሆን በቀላሉ ውሀ መከለስ ይቻላል:: ያላችሁበት ሀገር ህዝቡ በቁዋፍ ነው:: ለማባላት ትንሽ ይበቃል እንኩዋንስ በቅርብ ርቀት ጅቦቹ የሆነ ስጋ ሜንጦ ላይ ባንጠለጠሉበት ሀገር:: እልክ ደሞ ቤት አይገነባም:: አገር ገብታችሁ በቅርብ ያገራችሁን አየር እየተነፈሳችሁ መልካም ፍሬ ዝሩ ብትባሉ ጭራሽ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ እያላችሁ ህዝቡን ግራ አጋባችሁትና ትረፉት? ምናለ ባልገባችሁ ኖሮ: እጅግ ከልቤ አፈርኩባችሁ:: ላትሰሙኝ መድከሜ:: ግን ለራሴው ጤንነት ከሚልም ነው ነገሩ::

ለዶር አቢይና ቲም ለማ!

ሳስበው እነዚህን ሰዎች ንቀው ይለፉ:: ከነሱ አታካሮ የሚጎዳው ህዝቡ ነውና:: ጉልበቱን ስታገኙ ግን ሀይ በሉዋቸው በህግ:: ያለው ህገአራዊቱም ቢሆን እነዚህን ልክ ለማስገባት አያንስምና:: ይህው ነው: ከሰማችሁ::


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV