አርበኞች ግንቦት 7 የአማራ ገበሬዎችን እየመዘገበ ነው ።

አርበኞች ግንቦት 7 የአማራ ገበሬዎችን እየመዘገበ ነው

~”ምንም ዓይነት ስልጠና ሳይሰጡ የኛ ሰራዊት ስለሆናችሁ የመሳሪያ ብዛት እና የመሳሪያ ቁጥራችሁን አስመዝግቡ በእኛ በኩል ከመንግስት ጋር እየተወያየን ስለሆነ ህጋዊ ያልሆነውን መሣሪያ አስመዝግበን ህጋዊ ልናስደርግላችሁ ነው” በማለት መዝግበውናል ብለዋል።”

ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ እንደዘገበው

በወገራ ወረዳ የሚገኙ የታጠቁ ገበሬዎች አርበኞች ግንቦት ሰባት “ስንጠራቹህ ትመጣላቹህ” በማለት አባልነትን የሚገልፅ መታወቂያ በመስጠት እየመዘገባቸው መሆኑን ገለፁ

” ምንም ዓይነት ስልጠና ሳይሰጡ የኛ ሰራዊት ስለሆናችሁ የመሳሪያ ብዛት እና የመሳሪያ ቁጥራችሁን አስመዝግቡ በእኛ በኩል ከመንግስት ጋር እየተወያየን ስለሆነ ህጋዊ ያልሆነውን መሣሪያ አስመዝግበን ህጋዊ ልናስደርግላችሁ ነው” በማለት መዝግበውናል ብለዋል።

በተጨማሪም በሀገር ፍቅር ስሜት ስንታገል የነበርን የእንቃሽ አርበኞችንና አርሶ አደሮችን ቤት ንብረታችንና ልጆቻችን ትተን ወደ አግ 7 ካምፕ እንድንቀላቀል ከመጠየቅም ባሻገር ለዋስትና የሚሆን ነው በማለት መታወቂያ ሰጥተውናል ብለዋል።

የግል መሳሪያችንና የመሳሪያ ቁጥራችን እየመዝገቡ ህጋዊ እናስደርግላቹሀለን ቢሉም አውርዱ ላለመባላችንና በተለያየ ወንጀል በማሳበብ ላለመታሰራችን ግን ምንም ዓይነት ዋስትና የለንም፣እንሰጋለንም በማለት አንዳንድ ተመዝጋቢዎች ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በቋራ ወረዳም ገንዘብ እየሰጡ በግል የታጠቁ አርሶ አደሮችን እየመዝገቡ እንዳለም ከስፍራው ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።