የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መጋለጣቸው

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ከኦሮሚያ ክልል ጋር የሚያገናኘው መንገድ በጸጥታ ችግር ለዓመታት በመዘጋቱ፣ የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች ለማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መጋለጣቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልዑካን ቡድን መናገራቸው ምክር ቤቱ ገልጧል፡፡ ይታወቃል። በውይይቱ ወቅት፣ በክልሉ የሪፈራል ሆስፒታል ባለመኖሩ የክልሉ ነዋሪዎች ወደ አጎራባች ክልሎችና አዲስ አበባ በመሄድ ለከፍተኛ ወጪ እየተዳረጉ መሆኑን አውስተዋል ተብሏል። ነዋሪዎቹ፣ መንግሥት በክልሉ ውስጥ አንድ ሪፈራል ሆስፒታል እንዲገነባላቸው መጠየቃቸውንም መረጃው አመልክቷል።