የኮሚሽነር አበረ አዳሙ ህልፈተ ህይወት ምክንያት የልብ ጡንቻ መጎዳት ነው – ዶ/ር ሀብታሙ የእኔአባት ( ህክምና የሰጧቸው ስፔሻሊስት ሀኪም)


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኮሚሽነር አበረ አዳሙ ህልፈተ ህይወት ምክንያት የልብ ጡንቻ መጎዳት መሆኑን የህክምና ርዳታ ያደረጉላቸው ሀኪም ነገረውናል
(ኢ ፕ ድ) – በድንገተኛ ህመም ምክንያት ዛሬ ህይወታቸው ያለፈው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አበረ አዳሙ ህልፈተ ህይወት ምክንያቱ የልብ ጡንቻ መጎዳት መሆኑን ህክምና የሰጧቸው ስፔሻሊስት ሀኪም ነገረውናል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያነጋገራቸውና ለኮሚሽነር አበረ አዳሙ ህክምና የሰጡት በድሪም ኬር ጠቅላላ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ሀብታሙ የእኔአባት እንደገለጹት፤ ኮሚሽነሩ ጠዋት ላይ ለህክምና ወደ ሆስፒታሉ ሄደዋል።
የጤናቸው ሁኔታ ከበድ ያለ ስለነበር በፍጥነት ወደ ድንገተኛ ህክምና መስጫ ክፍል እንዲገቡ ተደርጎ አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎላቸው የልብ ህመም ምልክቶች ተገኝቶባቸዋል ብለዋል።
No photo description available.እንደ ዶክተር ሀብታሙ ገለጻ፤ ኮሚሽነር አበረ ልብ ላይ የታየውን ጥርጣሬ በተደጋጋሚ የህክምና ምርመራ ማረጋገጥ ስለሚገባ ሁለት ጊዜ የኢሲጂ ምርመራ ተደርጎላቸዋል፤ በተጨማሪም ሌሎች ከዚሁ ጋር የተያያዙ ምርመራዎች ተደርጎላቸዋል። ውጤቱም “myocardial infarction” መሆኑ ተረጋግጧል። ይህም ወደልባቸው የሚሄዱ የደም ስሮች ተዘግተው ስለነበር የልባቸው ጡንቻ ከሚጠበቀው በላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የምርመራ ውጤቱ አሳይቷል።
በዚህ መሀል ኮሚሽነር አበረ አዳሙ በተደጋጋሚ ራሳቸውን እየሳቱ ይነቁ እንደነበር የገለጹት ዶክተር ሀብታሙ፤ የልብ ጡንቻ ጉዳታቸው ከፍ ያለ ስለነበር አይሲዩ ወዳለበት የባህር ዳር ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ወደሆነው እንዲሄዱ በመወሰን ወደ ጥበበ ግዮን ሆስፒታል ተወሰደዋል ነው ያሉት።
ለኮሚሽነሩ ህልፈተ ህይወት ዋናው ምክንያት የልባቸው ጉዳይ ቢሆንም በወቅቱ ወደ ሆስፒታል ሲመጡም የስኳር መጠናቸው ከ400 በላይ ደርሶ እንደነበር ዶክተር ሀብታሙ ለኢፕድ ገልፀዋል።
No photo description available.