ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት አስተዋጽኦ ያበረከቱ የኢትዮጵያ ወታደሮች የክብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኑ፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) ስር የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኑ፡፡
ሽልማቱ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች በሶማሊያ በነበራቸው የአንድ አመት ከስድስት ወር ቆይታ በሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን በተደረገው ጥረት ላደረጉት አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት ያለመ መሆኑን አሚሶም አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያውያን ወታደሮቹ አልሸባብን ለመደምሰስ በተካሄደው ዘመቻ ከጂቡቲ እና ከሶማሊያ ወታደሮች ጋር በበለተወይኒ ሴክተር አራት ተሰማርተው ግዳጃቸው የተወጡ ናቸው፡፡
በአሚሶም የጂቡቲ ጦር አዛዥ ኮሎኔል አብዲራህማን ሃሬድ፥ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች የሶማሊያን ደህንነት ለማስጠበቅ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
አያይዘውም ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት ጊዜ፣ ጉልበትና ህይወታቸውን ለሰጡ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ያላቸውን ክብር ገልጸዋል በማለት ፋና ቲቪ ዘግቧል፡፡