በዐማራ ላይ ጀኖሳይድ የፈጸሙ ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ሂደት እየተካሄደ ነው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በዐማራ ላይ ጀኖሳይድ የፈጸሙ ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብ ሂደት እየተካሄደ ነው

በተቀነባበረና በተናበበ መልኩ በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች ውስጥ በአብይ አህመድ አዝማችነት በዐማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ የሚገኘውን ጀኖሳይድና የዘር ማጥፋት ለማስቆምና ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅረብ ለጠበቆች የሚከፈል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ጥረትን ማንኛውም አማራ መደገፍ ይገባዋል። በተለይም በዛሬው የትንሳዔ በዓል ላይ በግፈኞች የታረዱትን አማራዎች እያሰብን ደማቸው ደመ ከልብ ሆኖ እንዳይቀር የተጀመረውን የክስ ሂደት በገንዘብ መደገፍ የተቀደሰ ተግባር መሆኑን መገንዘብ ይገባናል።

በርካታ የአማራ እርጉዝ ሴቶች በጬቤ ማህፀናቸው እየተሰነጠቀ ጽንሳቸው ሜዳ ላይ ተጥሏል። በርካታ ሴቶች ጡታቸው ተቆርጧል። ብዙ ወንዶች ተሰልበዋል። ወንድ፣ ሴት፣ ክርስቲያን፣ ሙስሊም፣ ሽማግሌ፣ ወጣት ሳይለይ ሁሉም አማራ እየታደነ ተጨፍጭፏል። አማራዎች ከተገደሉ በኋላ እንኳን አስከሬናቸው እንደ ቁሻሻ በግሬደር ተዝቆ ቁሻሻ መጣያ ውስጥ ተጥሏል። ይህንን እያያና እየሰማ ዝም የሚል ህሊናው ይፍረደው ከማለት ሌላ ምንም ማለት አይቻልም። በዚህ ጊዜ ቢያንስ ቢያንስ በገንዘብ ለሚደረግ አስተዋጽኦ አለመሰታፍና ሰምቶ ማለፍ ጊዜ ሲቀየር፣ የነበረው እንዳልነበረ ሲሆን፣ የወጣው ሲወርድና ታሪክ ሲገለበጥ ለዘመናት የማይሽር የአእምሮ ቁስል ጥሎ ያልፋልና እባካችሁ እጃችሁ ይፈታ! ገንዘብ ለማዋጣት እዚህ ላይ ይጫኑ። https://www.gofundme.com/f/orthodox-tewahdo-against-genocide-in-ethiopia?utm_source=customer&utm_medium=copy_link&utm_campaign=p_cf+share-flow-1