በድሬደዋ በጣለው ከበድ ዝናብ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


May be an image of outdoorsበድሬደዋ ከተማ ዛሬ ጠዋት ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የአንድ ድርጅት አጥር ግንብ ፈርሶ በሶስት መኖሪያ ቤቶች ላይ በመውደቁ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ::
በአደጋው ህይወታቸው ካለፈው ውስጥም አንድ የሶስት ወር ጨቅላ እና እንዲሁም የሁለትና የአምስት አመት ህፃንናት ይገኙበታል::
ዛሬ ከረፋዱ ሁለት ሰአት ጀምሮ ባለማቋረጥ ከአራት ሰአታት በላይ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ በድሬደዋ ከተማ ቀበሌ 03 ሸመንተሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ ስድስት ሰአት ገደማ የባሻንፈር ትሬዲንግ ድርጅት እስከ ሀምሳ ሜትር የሚጠጋ የአጥር ግንብ በግንቡ ዙሪያ ባሉ ሶስት የተለያዩ መኖሪያ ቤቶች ላይ ፈርሶ በመውደቁ በቤቱ ውስጥ የነበሩ ዘጠኝ ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የኮሚሽኑ የህ/ግንኙነት ዋና ክፍል ሃላፊ ም/ኢ/ር ባንታለም ግርማ ገልፀዋል::
May be an image of ጌቱ በቀለ በዳዳ, standing and sittingሃላፊው አያይዘውም ከሟቾች ውስጥ አንዲት አራስ እናት ከሶስት ወር አራስ ጨቅላ ልጇን ባለቤቷ ጋር ህይወት ሲያልፍ አንድ የሁለት አመት እና አንድ አምስት አመት ህፃናን በአደጋው ህይወታቸው አልፏል ብለዋል::
የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በአደጋው በደረሰው ህልፈት ህይወት የተሰማውን ልባዊ ሀዘን ገልፀው በድሬደዋ ከተማ ከወትሮው በተለየ መልኩ ዝናብ በከፍተኛ ሁኔታ እየጣለና በቀጣይ ቀናትም ይሄው ተጠናክሮ የሚቀጥልና የጎርፍ አደጋም ሊያስከትል የሚችል ስለመሆኑ ቤሄራዊ ሜትሮሎጂ የገለፀ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መላው ህብረተሰብ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግም ም/ኢ/ር ባንታለም ግርማ ጨምረው አሳስበዋል::
ምንጭ፦ የድሬደዋ አስተዳደር ፓሊስ ኮሚሽን
May be an image of outdoors
May be an image of one or more people, people standing and outdoors