በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን እና እርስ በእርስ መከባበር እና መዋደድ እንዲኖር በማሰብ በዓሉን ማክበር እንደሚገባ የኃይማኖት አባቶች አሳሰቡ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ክርስቲያኑ ምዕመን የትንሳኤን በዓልን ሲያከብር ለዓለም ሰላም በመጸለይ መሆን እንዳለበት የኃይማኖት አባቶች አሳሰቡ:: በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን እና እርስ በእርስ መከባበር እና መዋደድ እንዲኖር በማሰብ በዓሉን ማክበር እንደሚገባ አባቶች ጠቁመዋል።
EBC : የትንሣኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ድህነትን ለሰው ልጆች ሁሉ እንዳስገኘ የገለጹት የኃይማኖት መሪዎቹ ሁሉም ክርስቲያን ለዓለም ሰላም በማሰብ እና በመጸለይ በዓሉን ሊያከበር እንደሚገባ አሳስበዋል።
የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኃይማኖት አባቶች ኢየሱስ ክርስቶስ በስልጣነ ኃይሉ ሞትን ድል አድርጎ ለሰው ልጅ መዳን ምክንያት መሆኑን አስታውሰዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ ያሳየው ፍቅር ምዕመናን በዚህ ምድር ሲኖሩ ሊኖሩበት እና ሊመሩበት የሚገባ የሕይወት መስመር መሆኑንም የኃይማኖት አባቶች ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን እና እርስ በእርስ መከባበር እና መዋደድ እንዲኖር በማሰብ በዓሉን ማክበር እንደሚገባ አባቶች ጠቁመዋል።
በዚህ በዓል ላይ ለተቸገሩ በመርዳት፣ ለታረዙ በማልበስ እና የታመሙትን በመጠየቅ ፍጹም የሰው ልጅ ባሕርይን በመተግበር ማክበር እንደሚገባ የኃይማኖት አባቶቹ አሳስበዋል።