የአፋር እና የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት በሰላም ሚኒስትር ሰብሳቢነት ነውስምምነት ደረሱ

የአፋር እና የሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት በርዕሳነ መስተዳድሮቻቸው የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቀበሌዎች የተፈጠሩ ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
ርዕሳነ መስተዳድሮቻቸው በሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሰብሳቢነት ነው ዛሬ ስምምነት ላይ የደረሱት፡፡
በሰላም ሚኒስቴር የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮችና የፌደራል መንግስት የጸጥታ አካላት በተገኙበት በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ቀበሌያት የተከሰቱ ግጭቶችን በአፋጣኝ ለማስቆምና በቀጣይ ችግሮችን ለመፍታት መስማማታቸውንም ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
No photo description available.