የኢትዮጵያውያን ክትባት በቨርጂኒያ “15 ሺ ሰዎችን ከትበናል”

በዩናይትድ ስቴትስ የኮቪድ ክትባት አሰጣጥ ሂደት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ክትባቱን ለማግኘት የተለያዩ መስፈርቶችና የጊዜ ቅደም ተከተሎች ያሉት ሲሆን እንደየ ክፍለ ግዛቶቹ ይለያያል፡፡ እዚህ ቨርጂኒያ ውስጥ ግን የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ አባላት ምንም ዓይነት ምዝገባና ወረፋ መጠበቅ ሳያስፈልጋቸው ከየትኛውም አካባቢ የመጡም ቢሆን፣ መታወቂያና የመድን ወይም ኢንሹራንስ ካርዳቸውን ብቻ በመያዝ ክትባቶቹ …