በአባይ ወንዝ «የታላቁ ሕዳሴ ግድብ» የኪንሻሳው ንግግር ያለውጤት መጠናቀቁ ተገለጠ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኪንሻሳው ንግግር ያለውጤት መጠናቀቁ ተገለጠ
Meetings between Egypt, Ethiopia, and Sudan to re-launch negotiations over  GERD resume Monday - Politics - Egypt - Ahram Onlineበአባይ ወንዝ «የታላቁ ሕዳሴ ግድብ» ምክንያት የሚወዛገቡት ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ኪንሻሳ-ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ውስጥ ያደረጉት ንግግር ያለስምምነት መቋጨቱ ተዘገበ። የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር ቃል አቀባይ አህመድ ሐፌዝ ኢትዮጵያ በድርድሩ ወቅት የዩናይትድ ስቴትስ፣ የአውሮጳ ኅብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪቃ ኅብረት ሚናን ውድቅ አድራጋለች ማለታቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በጉዳዩ ላይ ወዲያው አስተያየት አለመስጠታቸውንም የዜና ምንጩ ጠቅሷል። ሮይተርስ በበኩሉ ለኢትዮጵያ የውኃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚንሥትር ስለሺ በቀለ የላከው የአጭር ጽሑፍ መልእክት እና የስልክ ጥሪ ወዲያው ምላሽ እንዳላገኘ አትቷል።
የወቅቱን የአፍሪቃ ኅብረት የሊቀመንበርነት ሥልጣን በያዘችዉ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሸምጋይነት የተደረገዉ የሦስቱ ሃገራት ንግግር ከወራት በኋላ የተደረገ ነበር። ኢትዮጵያ ንግግሩ በአፍሪቃ ኅብረት ጥላ ስር ብቻ እንዲደረግ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ዐስታውቃለች። የግድቡን ኹለተኛ ዙር የውኃ ሙሌትም ከፊታችን ባለው የክረምት ወራት ለማከናወን ማቀዷን ገልጣለች።