ወለጋ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። የዞኑ አስተዳደር የሟቾችን ቁጥር ወደ 8 ዝቅ በማድረግ ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጧል። በዞኑ የደንጎሮ እና ቢላ ወረዳዎች በደረሰ ዘርን መሰረት ያደረገ ነው በተባለለት ጥቃት ሕይወታቸውን ካጡት በተጨማሪ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውና የተፈናቀሉ እንዳሉ ነዋሪዎቹ ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል።

« ከቤተክርስትያን 6 ሞቱ እንደገና የሆነች ከተማ አለች ውባንች የምትባል እዚያ ላይ 6 ሞቱ ፤ 12 ሆኑ። ሕጻናቶች የ3 ዓመት የ4 ዓመትም አሉ ፤ እንደገና አንዲት ሴት ደግሞ ሁለት ልጆች ይዛ አድራሻዋ ጠፋን። አንድ የ12 ዓመት ልጅም ጠፋን ፤ ማርከው ይዘዋቸው ሄደው ይሆን፤ እና ጫካ ውስጥ ነው ያለነው።»ጥቃቱ ኦነግ ሸኔ የተባለው ታጣቂ ኃይል መፈጸሙን የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ደቻሳ ተናግረዋል። በጥቃቱ ከኅብረተሰቡ ፣ ከመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና ከታጣቂ ቡድኑ በድምሩ ስምንት ሰዎች መገደላቸውን አቶ በቀለ ገልጸዋል።

« ትናንት ወደ 15 የሚሆኑ ሚሊሾች እዚያ ተደራጅተው ባሉ ላይ ተኩስ ከፍታ ወደ 3 ሚሊሻ እና ከህብረተሰቡ ደግሞ ወደ 3 ሰዎች መትታ ገድላለች። እነርሱም 2 የኦነግ ሸኔን ገድለዋል።»ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት ስለደረሰ የአካል እና የንብረት ጉዳት የዞኑ አስተዳዳሪ በዝርዝር ያሉት ነገር እንደሌለ የባህርዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን ዘግቧል። ጥቃቱን በፈጸመው የታጣቂ ቡድን ላይ መንግስት እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ግን አስተዳዳሪው ገልጸዋል። DW