በሌሎች ሃገራት የታየው የኮሮና እልቂት በኢትዮጵያ ይደገማል የሚል ከፍተኛ ስጋት አሳድሯል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


«በሌሎች ሃገራት የታየው እዚያም እንዳይደገም ሁሉም ወገን ኃላፊነት አለበት»

ኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ 19 የሚያዘው ሰው ቁጥር እየተበራከተ መሄዱ አሳሳቢ መሆኑ እየተነገረ ነው። ቀደም ባሉት ወራት በዋና ከተማ አዲስ አበባ በተሐዋሲው የሚያዙት ሰዎች ቁጥር መብዛቱ ቢነገርም አሁን ይኽ ተቀይሮ በተለያዩ የክልል ከተሞችም ተመሳሳይ ሁኔታ መኖሩን የሚመለከታቸው ይገልጻሉ። ወረርሽኙ የዛሬ ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ በታወቀ ጊዜ የታየው መደናገና ጥጥንቃቄ  ውሎ አድሮ በሌሎች ሃገራት የሆነው አስደንጋጭ ክስተት ባለመምጣቱ ወደመዘናጋት እንደወሰደ የሚናገሩ አሉ። ሕዝብ የሚሰባሰብባቸው የተለያዩ መድረኮች በዘፈቀደ መካሄድ፤ የተጀመሩ የመከላከያ ጥንቃቄዎችም በዚያው መንገድ አለመቀጠላቸው አሁን ከሦስት ተመርማሪዎች አንዱ በተሐዋሲው የመያዙን ውጤት እንዳመጡትም ያመላክታሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው መዘናጋትና የኮሮና ተሐዋሲ መዛመት እንዲሁም ኅብረተሰቡ ሊያደርገው የሚገባውን ጥንቃቄን አስመልክቶ ውይይት አካሂደናል። ሙሉ ውይይቱን የድምጽ ማዕቀፉ በመጫን ያድምጡ። DW Amharic