የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ 15 የትግራይ ክልል ተወላጆች ከደቡብ ሱዳን አንመለስም አሉ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ደቡብ ሱዳን ውስጥ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ 15 የትግራይ ክልል ተወላጆች« ለህይወታችን ያሰጋናል» በሚል ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አለመፍቀዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትናንት አስታወቀ።

የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት 169 የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊቶች በተለመደው አሰራር መሠረት ከጁባ እንዲወጡ ተደርገው በአዲስ ሰራዊት ይተኩ ነበር።

ይሁንና 15 የሰራዊቱ አባላት ከጁባ ኤርፖርት ለመሳፈር ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ስቴፈን ዱጃሪክ « ዓለም አቀፍ ጥበቃ የሚያስፈልገው ማንኛውም ሰው ጥገኝነት የመጠየቅ መብት አለው።» ሲሉ መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና ምንጭ AFP ዘግቧል።

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ሁኔታውን “ተገንዝቦ” ጥገኝነት መጠየቅ በፈለጉት የሰራዊት አባላት ጉዳይ ላይ ከደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ጋር እየመከረ ነውም ተብሏል።