በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ግጭቶች መኖራቸውንም የየአካባቢው ነዋሪዎች እያስታወቁ ነው።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


DW : ከተለያዩ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመምንጫ ተቋማት ወደ ትግራይ የተዘረጋው መስመር በመቋረጡ መላው ትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተቋረጠ ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል። የኤሌክትሪክ ኃይል በመቋረጡ ምክንያት ርዕሠ-ከተማ መቀሌን ጨምሮ በመላዉ ትግራይ የሚገኙ ተለያዩ አገልግሎት መስጪያ ተቋማት ሥራቸዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለማቆም ተገድደዋል። የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ እንደሚለው ወትሮም የንፁሕ የመጠጥ ውኃ እጥረት ያልተለየው የመቀሌ ሕዝብ ሰሞኑን ደግሞ በቦቴ የሚመላለስ አንድ በርሜል ውኃ እስከ ሰማኒያ ብር ለመግዛት እየተገደደ ነው። በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ግጭቶች መኖራቸውንም የየአካባቢው ነዋሪዎች እያስታወቁ ነው።