ጥብቅ ሚስጥር የያዘው የታህሳሱ የደብረጽዮን ኢሜይል

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

በታህሳሱ (December 2017) የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ላይ የተከናወነ ነበር። የአገሪቷ ወሳኝ ምዕራፍ መወሰኛ ስብሰባ፡፡ የለማና የገዱ ቡድን እየተጠናከረ ሲመጣ ትህነግ ስብሰባው ውስጥ ቁጭ ብሎ የሙስና ወንጀል በኦህዴድና በብአዴን ስራ አስፈጻሚዎች ላይ በሰፊው ይፈልግ ነበር። ደብረጽዮን ቀናውና በአዲስ አበባ ከንቲባ ደሪባ ኩማ መስተዳደር በግፍ የተባረረው የቀድሞ አማካሪና የአሁኑ የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ (Harvard University) ተመራማሪ Dec 17, 2017 ቀን ኢሜይል ጻፈ። በሙስና ሰበብ ለማምበርከክ የተፈለገው ደግሞ የአዲስ አበባውን ከንቲባ ደሪባ ኩማ ዋነኛነት ነበር። ኢሜይሉ እንደሚያሳየው የአዲስ አበባ ትራንስፖር ቢሮ ሃላፊው የዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ስም የተጠቀሰ ሲሆን ከዚህ ግለሰብ ጋር በተያያዘ ከንቲባው በሚከተሉት ሙስናዎች በከፍተኛ ሁኔታ በሰራተኞቹ ይታማ ነበር።

  1. በ850 አውቶቢስ ግዢና ከአለም ባንክ የተገኘው የ300 ሚሊየን ዶላር ብድር አፈጻጸም
  2. ከንቲባው በሚመራው በትራንስፖርት ቢሮ ስር የትራንስፖርት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በማቋቋምና ከንቲባው ራሱን የጽ/ቤቱ የቦርድ ዳሬክተር በማድረግ ጠያቂና ተጠያቂ እንዳይኖር በማድረግ በየአመቱ ከ600 ሚሊየን ብር በጀት በላይ ኦዲት ሳይደረግ ለዝርፊያ አመቻችቶ ስላዘጋጀ።

ስለሆነም ፈስ ያለበት መዝለል አይችልም እንደሚባለው በስብሰባው ወቅት ከንቲባ ደሪባ ለትህነግ (ህወሃት) ወግኖ በለውጥ ሃይሉ (የለማና ግድዱ ቡድን) ላይ ከፍተኛ ሂስ ሲያወርድ ነበር። ደረጀ ገርፋ በትክክል እንዳስቀመጠው ለግብ የሚሆኑ ኳሶች ለነደብረጽዮን ያቀብል ነበር። የለውጡ ቡድንም ቂም ይዞበት ስለነበር ስልጣን ከያዘ በኋላ ደሪባ ኩማን ከስልጣን ለማራቅ አምባሳደር አድርጎ በመሾም ከፖለቲካው በጡረታ አስወጥቶ ታከለ ኩማን በከንቲባነት ሹሟል። በሙስና የሚጠረጠረው ዶ/ር ሰለሞን የታከለ ምክትል ሆኖ እንዲቀጥል ተደርጓል።