በ25ኛው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ማሻሻያ እንደማይተገብሩት ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ገልጸዋል


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

የትራምፕ ደጋፊዎች ከፈጸሙት የአመጽ ድረጊት ጋር በተያያዘ ፣ የአሜሪካ ም/ቤት ፕሬዝዳንቱ በ25ኛው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ማሻሻያ መሰረት ከስልጣን እንዲወርዱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ፣ ሀገሪቱን በአግባቡ መምራት ያልቻለ ፕሬዝዳንንት ከስልጣኑ ተነስቶ ምክትሉ መሪነቱን እንዲረከብ የሚደነግገውን 25ኛውን ማሻሻያ እንደማይተገብሩት ገልጸዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንቱን በኢምፒችመንት ከስልጣን ለማውረድ ዝግጅት ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ አመጽ በመቀስቀስ ወንጀል ፕሬዝዳንቱን ለመክሰስ ዛሬ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በአሜሪካ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ኢምፒችመንት የሚካሄድባቸው መሪ ያደርጋቸዋል፡፡

ትራምፕ ከኋይት ሀውስ ለመውጣት የቀራቸው 1 ሳምንት ቢሆንም ፣ ፕሬዝዳንቱ በኢምፒችመንት እንዲነሱ ባለቀ ሰዓት ሩጫ መጀመሩ ፣ በዋነኛነት ከዚህ በኋላ ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳይቀርቡ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡ (አል ዓይን)