መተከል ምስኪኑ ህዝብ የሚታጨደዉ መንግስት ስፖንሰር በሚያደርገዉ ህቡእ አደረጃጀት ነዉ።


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
ግዮን ፋንታሁን – መተከል መንግስት ስፖንሰር የሚያደርገዉ ጭፍጨፋ ነዉ እየተካሄደ ብለን ከተናገርን ቆይተናል። ፕሮጀክቱ የመተከል ህዝብ ተያይዞ እንዲጠፋ የሚያደርግ ነዉ። ህዝብ እየተጨፈጨፈባቸዉ ያሉ ቦታወችን ለተመለከተ ከከተሞች ወጣ ያሉና ለሰፋፊ እርሻዎች ምቹ የሆኑ ቦታዎች ናቸዉ።
መተከል ከቀዩ በተጨማሪ ጉምዞቹም እያለቁ ነዉ። በቀዩ ስም የተደራጀ ህቡ ሀይል በየጫካዉ እየረፈረፋቸዉ ይገኛል። አብዛኞቹ በሳታላይት ከተሞች አካባቢ የነበሩ ጉምዞች ቤታቸዉ ተቃጥሏል። ከሞላ ጎደል ጉምዞቹ ጫካ ገብተዋል። እናቶች፣ ህፃናት በገዳይ ቡድኑ ጅምላ ግድያ፣ በርሃብና በበሽታ እያለቁ ነዉ።
እነሱ የሚነገራቸዉ ቀዩ እየገደላቸዉ እንደሆነ ነዉ። የጉምዞችን ሬሳና የተቃጠለ ቤት በህቡ የተደራጀዉ ቡድን በፎቶና በቪዲዮ እየቀረፁ እንዲመለከቱ ያደርጋሉ። ቀዩን ጨፍጭፈዉ ደግሞ በሶሻል ሚዲያ አሰቃቂዉን ምስል ይረጩለታል። የመተከል ህዝብ ቀይና ጥቁር እየተባባለ ቂምና በቀል እየቆጠረ ነዉ። እርስ በርሱ የሚችለዉን ያክል እንዲጠራጠርና በፍራቻ ቆፈን ተይዞ አንድ አካባቢ ተሰባስቦ እንዲቀመጥ ይፈለጋል።
የመተከል ፕሮጀክት አላማዉ ግልፅ ነዉ። የተንጣለለዉን ድንግል መሬት መቀራመጥ ነዉ። ከጭፍጨፋ የተረፈዉን ተፈናቃይ መልሶ በማቋቋም ስም አንድ አካባቢ ቤት እየሰሩ መሰብሰብ የፕሮጀክቱ አላማ ነዉ።
የአባይ ግድብ መጠናቀቅ አካባቢዉን የቀለጠ የልማት ኮሪደር ማድረጉ አይቀሬ ነዉ። የፕሮጀክቱ ወደ መጠናቀቂያዉ መቃረቡ ደግሞ ምርታማ የሆነዉ አካባቢ የአይን ማረፊያ እንዲሆን አድርጎታል። ችግሩ ያለዉ ጉምዞቹ ጋ ብቻ አይደለም። መተከል የብልፅግና ፖለቲከኛ ከጥገኛ ባለሃብት ጋር አሰፍስፎ እየጠበቀዉ ያለ አካባቢ ነዉ። ገና ካሁኑ መተከል ጭዉ ያለ በረሃ ላይ በአስርሽ ካሬ ሜትር የሚቆጠር መሬት የተሰጣቸዉና ለማልማት ወቅት እየጠበቁ ያሉ ባለሀብቶች እንዳሉ እኔ መረጃዉ አለኝ። የመተከልን ፕሮጀክት በአኝዋክ ሞዴል ተመልከተዉ። ህዝብን በአሰቃቂ ጭፍጨፋ ታፈናቅለዉና መልሰህ አንድ አካባቢ ቤት ሰርተህ ታሰፍረዋለህ። ህዝብ ጥሎ የሸሸዉን ሰፊ መሬት በልማት ስም ትቸበችባለህ። በጥቂት አመታት ዉስጥ ከፊሉ መተከል ለዉጭ ባለሃብት፣ ከፊሉ ለብልፅግና አመራርና ጥገኛ ባለሃብት ሊሸነሸን ተዘጋጅቷል። ምስኪኑ ህዝብ የሚታጨደዉ መንግስት ስፖንሰር በሚያደርገዉ ህቡእ አደረጃጀት ነዉ።- ግዮን ፋንታሁን