በኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 20 ዓመታት ለሚገነቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች 107 ከተሞች ተለዩ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

በቀጣዮቹ 20 ዓመታት በኢትዮጵያ 107 የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገነቡባቸው ከተሞች የለየ ጥናት መቅረቡ ተገልጿል።

በጥናቱ የተለዩት ከተሞች ባላቸው የህዝብ ብዛትና ነባራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ በኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን የማርኬቲንግና ኮሚውኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ባህይሉ ከበደ ለሸገር ገልጸዋል።

ከተለዩት ከተሞች ውስጥ ሰባት ያህሉ ግንባታቸው በሶማሊ ክልል የሚደረግ ሲሆን ይህም በቅርቡ ጥናቱ እየተገባደደ የሚገኘውን የአይሻ ኢንደስትሪ ፓርክን ይጨምራል ብለዋል።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ አስራ ሦስት የሚሆኑ የኢንደስትሪ ፓርኮች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አስራ አንዱ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። ሁለቱ በሂደት ላይ የሚገኙ መሆናቸውን የሸገር ኤፍ ኤም ዘገባ ያሳያል።