አሉባልታዊና ሐሜተኛ ማህበረሰብ እየተገነባ ከመጣ የመዝቀጥ አሊያም የመበስበስ ክፉ አባዜ መምጣቱን ይጠቁማል፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

ፍላጐታችንን ያከበሩ በመምሰል ፍላጐታቸውን የሚያሟሉ ሰዎች አደገኞች ናቸው፡፡ ፀሐይ የሚሞቅ ውሻ ሁሉ ሞኝ አይደለም፡፡ አሉባልታዊና ሐሜተኛ ማህበረሰብ እየተገነባ ከመጣ የመዝቀጥ አሊያም የመበስበስ ክፉ አባዜ መምጣቱን ይጠቁማል፡፡ አሉባልታ የሚቆመው ግልፅነትና መረጃ ሰጪነት ሲከበር ነው፡፡የሌሎችን ግብና አዕምሮ ማማለልንና ማዘናጋትን የሚያውቁበት ሰዎች እንዳሉ አንርሳ! ተስፋ በመስጠት እንደዳማና እንደ ቼዝ ጠጠር (ወታደር) በፈለጉት አቅጣጫ ይገፉናል፡፡

ላዋለሁ የሚል ጅል ተኩላ  ምን ጊዜም አይጠፋም፡፡ ይህን ሁሉ የሚታዘብ ህዝብ እንዳለ የሚያውቅ ካለ የብልህም ብልህ ነው፡፡ በዚህ የተካኑ ሰዎችን በዐይነ – ቁራኛ ማየት ያባት ነው፡፡ ስሜትን ተቆጣጥሮ ደባና ሴራን ጠንቅቆ ማየትና በጠዋት መንቃት ተገቢ ነው፡፡ ድቀትና ዝቅጠት ሲያይል አሉባልታና ጥርጣሬ ይነግሳል፡፡

በእንዲህ ያለው ሰዓት አፍ – አዊ እየበረከተ፣ ልባዊና ተግባራዊ እየሳሳ ይመጣል፡፡ ይሄኔ መጠንቀቅ ይበጃል፡፡ የአንድ ነገር ዋጋ በዚያ ተገልግለን በምናገኘው ጥቅም አይለካም፡፡ ይልቁንም ያንን ነገር ለማግኘት በምንከፍለው መስዋዕትነት ነው የሚለካው፡፡ አገር እንገነባለን ስንል ይህን ብሂል አለመርሳት ነው፡፡ ይሆነናል የምንለውን ሰው መርጠን ስንሾምም ይህንን አለመዘንጋት ነው፡፡ ባለሙያው እያለ ስለዚያ ሙያ የሚያወራ ሲበዛ ጠንቀቅ ማለት ያሻል፡፡

ፕሮፓጋንዳ ብቻውን ሁሉን ጉዳይ አይጨርስልንም፡፡ አስተዋይ አመራር፣ አስፈፃሚና ተጠያቂነትን ገምጋሚ እንዲኖር ያሻል፡፡ ያ ደግሞ ግልጽነትን ልማድ የሚያደርግ መሆን አለበት፡፡ አሉባልታ የሚቆመው ግልፅነትና መረጃ ሰጪነት ሲከበር ነው፡፡በምንም ዓይነት ግን የፖለቲካ ትግልን እንደማይተኩልን ማሰብ ተገቢ ነው! የፖለቲካ ትግል ከሁሉም በፊት መደራጀትን፣ ተደራጅቶም መስዋዕትነትን፣ በሀገር ላይ ለውጥ የማየት ልባዊ ስሜትን ይጠይቃል! በተግባር ሳይሆን አሉባልታዊና ሐሜተኛ ማህበረሰብ እየተገነባ ከመጣ የመዝቀጥ አሊያም የመበስበስ ክፉ አባዜ መምጣቱን ይጠቁማል፡፡ ተግባራዊና የሚለውን የሚተረጉም ማህበረሰብ ካልፈጠርን ሟርት ይበዛል :: ምንሊክ ሳልሳዊ