የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የኦፌኮ አባል ከእስር ተለቀቁ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት እና ስነባህሪ ኮሌጅ ዲን እና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አባል ዶ/ር ሁሴን ከድር ከመንፈቀ ዓመት በኋላ ከእስር ተለቀቁ፡፡ ዶክተር ከድር ከታሰሩ በኋላ ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ በዋስትና እንዲለቀቁ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች ሳይከበሩ እንደቆዩ ጠበቃቸው አቶ ከድር ቡሎ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል…