ከአፍሪቃዉያን ለትራምፕ፤ አሁን ፀያፍ ስያሜ የሚገባዉ ማነዉ? 

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ሰሙኑን በአሜሪካ ትቅደም «America First» ፖለቲካቸዉ አሜሪካን ቁልቁል እየነድዋት መሆኑ እየተነገረ ነዉ። በአፍሪቃ ምንም በሚባል ደረጃ ወዳጅ ያላፈሩት ትራምፕ የአፍሪቃና ሃይቲ መጤዎቹን በማንቋሸሽ ተጠቀሙት የተባለው ፀያፍ አነጋገራቸዉ በአፍሪቃ ብዙዎችን አስቆጥቶ እንደነበር አይዘነጋም።…