ዶቼ ቨለ (DW) ፣ BBC ፣ ሮይተርስ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተሰጣቻው – የሮይተርስ የኢትዮጵያ ዘጋቢ ታገደች


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ መንግስት በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተሰማ።

እርምጃ እየተወሰደባቸው የሚገኙት ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ዓለም በተሳሳተ መንገድ እንዲያውቀውና በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲበረታ በማድረጋቸው ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 እንደተናገረው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ወቅታዊውን ሁኔታ በጥንቃቄ እንዲሁም በሞያዊ ስነ ምግባር እንዲዘግቡ ማሳሰቢያ ቢሰጣቸውም በእንቢተኝነት በቀጠሉት ላይ እርምጃ መወሰዱን አሳውቋል።

ዶቼ ቨለ (DW) ፣ BBC ፣ ሮይተርስ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከተሰጣቻው መካከል ይገኙበታል።

“ሮይተርስ” ከትላንትና ወዲህ በሀገር ውስጥ ያላቸው ዘጋቢ በኢትዮጵያ ጉዳይ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳታደርግ ፣ ዘገባዎችን ፣ ዜናዎችን እንዳትሰራ ሙሉ በሙሉ እንደታገደች የብሮድካስት ባለስልጣን ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።